https://t.me/tikvahethmagazine/20771
በቲክቫህ
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ ጽ/ቤት ሺሻ በማጨስ በማስጨስ እና በቁማር ቤቶች በህገ ወጥ ተግባር ላይ የተገኙ 63 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር በማዋል ከ400 በላይ የሺሻ ማጨሻ እቃዎችን ማስወገዱን ገልጿል።
በሺሻና በቁማር ቤቶች በቁጥጥር ስር ከዋሉት 63 ግለሰቦች መካከል 8ቱ ግለሰቦች በከፍተኛ የስርቆት ወንጀል የሚጠረጠሩ በመሆናቸው ጉዳያቸው በምርመራ ላይ እንደሆነ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል ገልጸዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉትን ግለሰቦች በቡታጅራ ከተማ ምክር ቤት በሺሻ ማጨስና ማስጨስ ወንጀል ላይ በወጣው ደንብና ቅጣት መሰረት እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አዛዡ ተናግረዋል።
የተያዙት የሺሻ ማጨሻ እቃዎችም፥ ህዝብ ሊማርበትና ሊመለከት በሚችል ሁኔታና ቦታ ቡታጅራ አርብ ገበያ አካባቢ በእሳት በማቃጠል ተወግዷል ሲል የዘገበው የከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው