በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አካባቢው አገልግሎት ለሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡ ፡
ጤና፥ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ከባህርዳር፥ኮምቦልቻ እና ደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አካባቢው ከሚገኙ የጤና ተቋማት ለተውጣጡ 25 ( ሃያ አምሰት ) የጤና ባለሙያዎች ማኅበረ-ስነልቦናዊ ድጋፍ እና የስነልቦና የመጀመሪያ ድጋፍ (Psycho-social support & Psychological first aid) ስልጠና በቀይ መስቀል ማሰልጠኛ ማዕከል በመሰጠት ላይ ነው፡ ፡
ስልጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን አላማውም በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና አካባቢው ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎት ለሚሰጡ ባለሙያዎች የእውቀት፥የክህሎት እና አመለካከት ክፍተቶችን በመሙላት ከስራቸው ጋር አቀናጅተው አገልግሎቱን እንዲሰጡ ለማስቻል ነው ፡ ፡
ማኅበሩ ከUNFPA ጋር በመተባበር በባህርዳር፥ኮምቦልቻ እና ደብረብርሃን ኢንዱሰትሪ ፓርኮች በመተግበር ላይ ባለው የስነ-ተዋልዶ ጤናና ፆታዊ ጥቃት መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮጀክት ታላሚዎች በሆኑት የፓርኮቹ ሴት ሰራተኞች ከሚኖርባቸው የስራ ጫና አንፃር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እነዲሆኑ በስፋት እየሰራ ይገኛል ፡