HDAMA

የአበሸብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የወባ ሳምንትን የአካባቢ ቁጥጥር ስራ በመስራት እያከበሩ ነው!

በደብረኤልያስ ወረዳ አበሸብ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤ/ት ተማሪዎች በጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር አስተባባሪነት እየተከበረ ያለውን የወባ ሳምንት ምክንያት በማድረግ በአካባቢያቸው ዉሃ ያቆሩና ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ቦታወችን በመረበሽ፣ በመበጥበጥ እንዲሁም በማፋሰስ እያከበሩ ነው፡፡