HDAMA

የአካባቢ ቁጥጥር ስራ አዊ ዞን አየሁ ጓጉሳ ወረዳ በደገራ ክላስተር አምበራ ጎጥ

ለወባ ትንኝ አመቺ የሆኑ ውሃ ያቆሩና ረግረጋማ ቦታዎችን በመለየት፣በማፋሰስና በማዳረቅ በወባ በሽታ አንድም ሰው እንዳሞት እናድርግ!ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር በአዊ ዞን አየሁ ጓጉሳ ወረዳ እየተገበረ ባለው የማህበራዊ ባህሪ ለውጥ ተግባቦት ፕሮጀክት በተደረገው የማህበረሰብ ንቅናቄ በደገራ ክላስተር አምበራ ጎጥ ማህበረሰቡ በአካባቢው የሚገኙ ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ውሃ ያቆሩና ረግረጋማ ቦታወችን በመለየት፣ በማፋሰስ፣ በማዳፈንና በማዳረቅ የአካባቢ ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡