HDAMA

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር በኮምቦልቻ ከተማ 03 ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ ለተንቀሳቃሽ ሴተኛ አዳሪዎች ማረፊያ የሚሆን ክፍል በቁሳቁስ አደራጅቶ አስረከበ፡፡

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር በኮምቦልቻ ከተማ 03 ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ ለተንቀሳቃሽ ሴተኛ አዳሪዎች ማረፊያ የሚሆን ክፍል በቁሳቁስ አደራጅቶ አስረከበ፡፡

ቋሚ መኖሪያ ለሌላቸውና ሌሊት ላይ በወሲብ ንግድ ለተሰማሩ ሴተኛ አዳሪዎች ቀን ቀን የሚያርፉበት ማረፊያ ክፍል አዘጅቶ አስረክቧል፡፡

ይህ ማረፊያ ተደራራቢ አልጋዎች፣ ማቀዝቀዣ፣ቴሌቪዥን፣ የጠረጴዛ ቴኒስ መጫዎቻ እንዲሁም የምግብ ማብሰያና የቢሮ ቁሳቁሶችን ያሟላ ነው፡፡

ይህ ማረፊያ ክፍል በጤና ጣቢያው ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይህም ታላሚዎቹ የጾታዊ ጥቃት ቢደርስባቸው ድንገተኛ የእርግዝና፣ የHIV እና ሌሎች የአባላዘር በሽታ ምርመራዎችን ፤ እንዲሁም የስነተዋልዶ ጤናና ምክር አግልግሎት ተረጋግተው እንዲያገኙ ለማስቻል ነው፡፡