HDAMA

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመተባበር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጋር በመተባበር የምግብና መድኃኒት አዋጅ ቁጥር 1112/2011 ውስጥ በተካተቱ ከትምባሆ ቁጥጥር ጋር ተያያዥነት ባላቸው አንቀጾች አተገባበር ሁኔታ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡በዚህ የውይይት መድረክ የጤና ሚንስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ ከፌደራል ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የተወከሉ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች፣ የህዝብ እንደራሴዎች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከአ/አ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ከአ.አ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች፣የሚዲያ ኃላፊዎችና ጋዜጠኞች አንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተገኝተዋል፡፡ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ባለስልጣን የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳግም አለማየሁ የትምባሆ ቁጥጥር አዋጅ ዋና ዋና ይዘቶችን ያቀረቡ ሲሆን የባለስለጣኑ ዋና ዲሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ ህጉ ከወጣ ጀምሮ የተከናነወኑ ተግባራትን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተወሰዱ የመፍትሄ ርምጃዎችን በተመለከተ አቅርበዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ በተሳታፊዎች ውይይት ተደረጓል፡፡ ህጉን በማስፈም ረገድ አበረታች ጅማሮዎች ቢኖሩም ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ክፍተቶች እንዳሉ በመድረኩ ተነስቷል፡፡ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር ትምባሆ በጤና ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የሚዲያና ኮምንኬሽን ፕሮጀክት አየተገበረ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡