logo

Dec 08 2023

በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ፣ሜሪላንድና ቨርጅኒያ ከተሞች የሚኖሩ የጎጃም መረዳጃ ዕድር አባላትና ደጋፊዎች በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች በጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በኩል ድጋፍ አደረገ፡፡

በአሜሪካን አገር ዋሽንግተን ዲሲ፣ሜሪላንድና ቨርጅኒያ ከተሞች የሚኖሩ የጎጃም መረዳጃ ዕድር አባላትና ደጋፊዎች በቅርቡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በደሴና ኮምቦልቻ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖቻችን ዕርዳታ እንዲውል በለገሱት 1.83 ሚሊዮን ብር ጤና፣ ልማትና ፀረወባ ማኅበር 2,700 የብርድ ልብሶችንና 26,400 የሚሆኑ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ፓዶችን በመግዛት ነሃሴ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ልኳል፡፡ማኅበሩ ይህ የሰብአዊ ርዳታ አገልግሎት ቀጣነይነት እንዲኖረው በትኩረት እየሰራበት ይገኛል፡፡

admin

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution