logo

Dec 08 2023

የጤና ልማትና ፀረ- ወባ ማህበር ከአሜሪካ ኗሪ የጎጃም እድር አባላትና ደጋፊዎች ጋር በመተባበር በደሴና ኮምቦልቻ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ1.83ሚሊየን ብር ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።ደሴ ፡ነሀሴ28/2013(ደሴ ኮሙዩኒኬሽን)

የጤና ልማትና ፀረ- ወባ ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ አበረ ምህረቴ አሜሪካ የሚኖሩ የጎጃም እድር አባላትና ደጋፊዎች በማስተባበር በደሴና ኮምቦልቻ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ፍላጎት በጠየቁት መሠረት የ1ሚሊየን 830ሺብር የሚያወጡ 2,700 ብርድልብስና 26,400 ለሴትች የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ለደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና አስተባባሪ አስረክበዋል። ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ቀድመን በመድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እርካታው ለረጅው ነውና ድጋፉ ይቀጥላል ነገር ግን በየቀኑ እየተፈናቀሉ የሚመጡት ቁጥር ለማስቆም መንግስት አሸባሪውን የትህነግ ቡድን በአጭር ጊዜ በመደምሰስ ሰላምን ማስፈን እንዳለበት ዶክተር አበረ ምህረቴ ተናግረዋል።የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና አስተባባሪ አቶ መሳይ ማሩ በአሁኑ ሰአት በሁለቱም ከተሞች ከ233,400 በላይ ተፈናቃዮች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ በደሴ በ12 ት/ቤት ጊዜያዊ መጠለያ 5700 ተፈናቃዬች ሲኖሩ ሌሎቹ ደግሞ በግለሠብ ቤት ተከራይተውና ወዳጅ ዘመድ ቤት የተጠለሉ መኖራቸውን ገልፀዋል።አቶ መሳይም በመንግስት በኩል የተለያዩ የምግብ እህሎችና አልሚ ምግብን እየረዳን ሲሆን ማንኛውም ረጅ ድርጅቶችና ግለሠቦች ሚያመጡትን ድጋፍ በቀጥታ ት/ቤት በመግባት መርዳት ሳይሆን ድጋፍ ፍትሀዊ ክፍፍልና ስርጭት እንዲኖረው እየተሠራ ሲሆን ወደ አንድ ማእከል በደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበያ ተቋም በመምጣት መስጠትና መከፋፈል ይኖርበታል ብለዋል+

admin

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution