logo

Dec 08 2023

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር አሜሪካ ሀገር ከሚኖሩ የጎጃም ዕድር አባላት ጋር በመተባበር ከሰሜን ወሎ ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች 1 ሚሊዬን 830 ሽህ ብር የሚያወጣ ብርድ ልብስና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ ነሀሴ፡28/12/2013

የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አበረ ምህረቴ ለህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ቡድን እንደገለፁት ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር በሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ድርጅቱ ቅድሚያ ለሰው ልጅ በሚል ሰብአዊነት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ የወባ ወረርሽኝን በመከላከል የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስን በመቆጣጠር በርካታ ስራዎችን ጨምሮ እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡ በኮምቦልቻ ከተማ በወጣቶች ዙሪያ የአቻ ለአቻ ፕሮጀክት በመቅረጽ የትምህርትና የማቴሪያል ድጋፍ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በኮሌጆች ሰፊ ስራ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡ እንደ ዶክተር አበረ ገለፃ ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በኮምቦልቻና በደሴ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች ድርጅቱ አሜሪካ ሀገር ከሚኖሩ የጎጃም ዕድር አባላትና ተባባሪዎች የተሰባሰበውን 1ሚሊዬን 830 ሽህ ብር ለ2 ከተሞች ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ድጋፉ 2,700 ብርድ ልብስ 26 ሽህ 400 የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘሪቱ ሁሴን በበኩላቸው ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር ወቅቱ ክረምት በመሆኑና አብዛሀኛው ተፈናቃይ ሴቶችና ህፃናት በመሆናቸው የተደረገው ድጋፍ ክፍተትን የለየ ነው ብለዋል፡፡ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመድ ከበደ ድጋፉን ለተፈናቀሉ ወገኖች አስረክበዋል፡፡ የተፈናቀሉ ወገኖችንም ጦርነቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ መኖሪያ አካባቢያችሁ ትመለሳላችሁ ብለዋል፡፡ ግለሰቦችና ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችም የተጀመረውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥ::

admin

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution