logo

Mar 13 2024

ጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በአማራ ክልል ተደራሽ ባልሆኑ 5 ዞኖች ለሚገኙ የጤና ተቋማት አስፈላጊ የሕክምና ምርቶች እና አቅርቦቶችን የማሰራጨት ስራ በተሳካ ሁኔታ ጀምሯል።

ማኅበሩ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ለዞኖች እና ወረዳ ጤና ተቋማት መድኃኒት እንዲያጓጉዝ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብ ፣ ምሰራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች ለሚገኙ 97 የጤና ተቋማት ከአባላቱ በተሰበሰበ ገንዘብ የፀረ-ወባ፣ የፀረ ኤች አይ ቪ፣ የቲቢ፣ የክትባት፣ አንቲ ባዮቲክ እና ሌሎች መድኃኒቶችን የማጓጓዝ ስራ እየሰራ ይገኛል::

በአካባቢው የተከሰተው ችግር እየተባባሰ በመምጣቱ እና የመንግሰት ተሽከርካሪዎች እንደልብ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ከላይ የተጠቀሱት የመድሃኒት ግብአቶችን በወቅቱ ማሰራጨት አልተቻለም፡፡

ይህ ጥረት በጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሰት ተቋማት፤ አለም አቀፍ የሰባዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት በጋራ ተረባርበን ለህብረተሰቡ ልንደረስለት ይገባል ሲል ጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

May be an image of text

See insights and ads

Boost post

Like

Comment

Share

admin

Leave A Comment

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution