logo

May 01 2024

ጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር 25ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በባህር ዳር በድምቀት አካሄደ፡፡

የጉባዔው አጀንዳዎች የ2015 በጀት ዓመት የክንውን ሪፖርት፤ የ2015 በጀት ዓመት የሒሳብ ምርመራ ሪፖርት፤ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የማኅበሩን አዲሱን ሎጎ ማጽደቅ ሲሆኑ በጉባዔው የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በማኅበሩ ዋና ዲሬክተር ክቡር ዶ/ር. አበረ ምህረቴ በተቋማዊ አቅም ግንባታ ተግባራት፣ አባላት ማበራከት፣ ገቢ ማጠናከር፣ የወባ መካላከልና ቁጥጥር፣ በሕፃናት እንክብካቤና ድጋፍ፣ በስነ-ተዋልዶና ኤች.አይ.ቪ መከላከል፣ በትንባሆ ቁጥጥር፣ በጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ቁጥጥር እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ በሚሉ ግቦች የተከፋፈሉ ዝርዝር ተግባራትን በዓይነት እና በመጠን፤ በዕቅድና ክንውን፤ እንዲሁም የበጀት እቅድና ክንውን ንፅፅር ጋር በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም በአቶ ስንታየሁ ሙሉጌታ ታደሰ የተመሰከረለት ኦዲተር የማኅበሩን የ2015 የበጀት ዓመት የሒሳብ እንቅስቃሴ በዝርዝር ለጉባዔው ታዳሚ አቅርበዋል፡፡

በጉባዔው ላይ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በዝርዝር ለውይይት የቀረበ ሲሆን እቅዱ የተዘጋጀው በመፈፀም ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ታሳቢ በማድረግና የማህበሩን ስትራቴጂክ እቅድ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው፡፡

በመጨረሻም የጉባኤው አባላት በቀረበው የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2016 በጀት እቅድ ላይ እንዲሁም በተነሱት አስተያየቶች በጥልቀት ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ የቀረቡለትን አጀንዳዎች አፅድቋል፡፡

+8

Boost post

Like

Comment

Share

admin

Leave A Comment

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution