logo

May 16 2024

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ለትምባሆ ቁጥጥር ፕሮጀክት ግንዛቤ ማስጨበጫ ያዘጋጃቸውን የኮምንኬሽን ስራዎች ለግምገማ አቀረበ፡፡

ማኅበሩ እየተገበረ ባለው የትምባሆ ቁጥጥር የሚዲያና ኮምንኬሽን ፕሮጀክት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተዘጋጁ ለማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የሚያገለግሉ አጫጭር ቪዲዮዎች እና የቢልቦርድና ስክሪን ግራፊክስ ስራዎች ለአጋር አካላት ለግምገማ አቅርቧል፡፡ እነዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ትኩረት ያደረጉት በምግብና መድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2011 መሰረት ከትምባሆ ጭስ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ፣ ትምባሆ የማይጨስባቸውና ክልከላ የተደረግባቸው ተቋማት ላይ ነው፡ ፡

በዚህ ዝግጅት ላይ የኢትዮጵያ መድኃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን፥ የአዲስ አበባ መድኃኒትና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ ማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ እንዲሁም በጊዜ ኦፐቲማክስ ተሳትፈዋል ፡፡

+8

Boost post

Like

Comment

Share

admin

Leave A Comment

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution