logo

May 23 2024

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር Chemonics International ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡ ፡

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር Chemonics International ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡ ፡

በአማራ ክልል ተደራሽ ባልሆኑ ዞኖች ለሚገኙ የጤና ተቋማት አስፈላጊ የሕክምና ምርቶች እና አቅርቦቶችን ለማሰራጨት ከ Chemonics International ጋር ተፈራረመ ፡፡

ጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በክልሉ አስፈላጊ የመድኃኒት አቅርቦቶችን ወደተለያዩ የጤና ተቋማት የማጓጓዝ እና ማሰራጨት ክፍተት በመኖሩ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ በቀረበለት ጥሪ መሰረት ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ስምምነቱም ደሴ፣ ባህርዳር እና ጎንደር ከሚገኙ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖች ወደ ጤና ተቋማት የፀረ-ወባ፣ የፀረ ኤች አይ ቪ፣ የቲቢ፣ የክትባት፣ አንቲ ባዮቲክ እና ሌሎች መድኃኒቶችን የማጓጓዝ እና ማሰራጨት ስራ እነደሆነ ተገልጿል፡፡

ማኀበሩ ከዚህ ቀደም ከራሱ ገቢ በአምስት ዞኖች ለሚገኙ 153 የጤና ተቋማት አስፈላጊ የመድኃኒት አቅርቦቶችን በማጓጓዝና በማሰራጨት 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ተደራሽ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

+8

Boost post

Like

Comment

Share

admin

Leave A Comment

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution