logo

Jun 28 2024

አጋር መፅሔት ዳግም ለህትመት በቃ

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ልሳን “አጋር” መፅሔት ዳግም ለህትመት በቃ

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረበዓል በማስመልከት ያሳተመውን 10 ሺህ ኮፒ መፅሔት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አስመርቋል።

በ1992 ዓም የማኅበሩ ልሳን በመሆን ቁጥር አንድ ህትመቱን ጀምሮ ለተከታታይ 8 ዓመታት የዘለቀው እና በመሃል  ህትመቱ ተቋርጦ የቆየው “አጋር” የተሰኘው መፅሔት ዳግም ወደ ህትመት ተመልሷል። በያዝነው ዓመትም የማኅበሩን የ25ኛ ዓመት ክብረበአል በማስመልከት የመፅሔቱ ልዩ ዕትም  በ10 ሺ ኮፒ ታትሟል ።

መፅሔቱም  በአማርኛና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀና 64 ገፆች ያሉት ሲሆን የማኅበሩን አምባሳደር የክቡር ዶ/ር ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን መልእክት ጨምሮ የተለያዩ ዓምዶችን  በመያዝ የማኅበሩን አመሰራረት፣ 25 አመታት ጉዞ፣ በአሁኑ ወቅት እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶች፣ አንባቢያንን ዘና የሚያደርጉ የስነ-ፅሑፍ ስራዎች እና የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ምስክርነቶችን አካቶ ይዟል።   

በዝግጅቱ ላይ የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር የክብር ዶክተር አበረ ምህረቴ የመፅሔቱን ህትመት አጠቃላይ ወጪ በመሸፈን አጋር ለነበረው FHI 360 እንዲሁም በበዓሉ አከባበር ሂደት ድጋፍ ላደረጉት አቢሲኒያ ባንክ እና ቡና ባንክ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። መፅሔቱም በኣመት አንድ ግዜ   ለህትመት እንደሚበቃ አስታውቀዋል። ማኅበሩ በአሁኑ ወቅት ከ 260 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ጠንካራ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መሆኑንም አክለው  ገልፀዋል።

በዚህ ጊዜ ይሄ ዝግጅት የተዘጋጀበት ምክንያት የወባ በሽታ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ተሳታፊዎች እና ሚዲያዎች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማሳሰብም ጭምር ነው።

+8

Boost post

Like

Comment

Share

admin

Leave A Comment

Location

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution