HDAMA

our journey

ሰኔ 21/199ዐ፡– በዚህ ዕለት ማታ የጐጃም ተወላጅ የሆኑት አቶ አበረ ምሕረቴ   በጐጃም ስለደረሰው የወባ ወረርሽኝና ያስከተለውንየሕዝብ   እልቂት መንግሥት ዝም ብሎ ማየቱን በመግለጽ የሐረር ተወላጅ   ለሆኑት ባለቤታቸው ለወ/ሮ ማሪያ  አብዱል ቃድር   ያወያዩአቸዋል፡፡ ወ/ሮ ማሪያም ባለቤታቸው ለሕዝባቸው    የሰሩትን ሥራ ይጠይቋቸዋል፡፡አልመለሱም፡፡ በተግባር   ለማሳየት ወሰኑ፡፡ለጓደኛቸው ለዶ/ር ይልቃል አዳሙ  ደወሉ፡፡   ቀጠለ፡፡

ሰኔ 28/199ዐ፡- በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ስምንት   ሰዎች ተገናኙ::

  1. አቶ አበረ ምሕረቴ

  2. ዶ/ር ይልቃል ኣዳሙ

  3. አቶ አሳያስ ተስፋው

  4. አቶ መኮንን ገበየሁ

  5. አቶ ጤናው አንዱዓለም

  6. አቶ ሽመልስ ቀፀላ

  7. አቶ ማኀፀንቱ ፈለቀ

  8. አቶ ይግረም አዳል

ለሚዲያ፣ ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ማሳወቅ በሚቻልበት መንገድ መክሮ እንዲያቀርብ አቶ አበረ ምሕረቴን፣ አቶ ኢሳያስ ተስፋውን፣ አቶመኮንን ገበየሁን፣ አቶ ጤናው አንዱዓለምን፣ አቶ ሽመልስ ቀፀላን በመምረጥ ለቀጣይ እሁድ ተቀጠረ፡፡

ሰኔ 3ዐ/199ዐ፡- ኮሚቴው  ተገናኝቶ  ጥናቶችን አዘጋጀ::

ሐምሌ 5/199ዐ፡- በአራት ሰዓት ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች    ተገኙ፡፡ኮሚቴው ጥናቱን አቀረበ፡፡የተጨበጠ መረጃ    ስላልቀረበ ለቀጣይ እሁድ እንዲቀርብ ተወሰነ፡፡

ሐምሌ 12/199ዐ፡- የምዕራብ ጐጃምን የወባ ሁኔታ የሚያሳይ ተጨባጭ ሪፖርት ቀረበ፡፡ማኀበር ማቋቋም ወሳኝ መሆኑ ታመነ፡፡

ነሐሴ 17/199ዐ፡- በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አዳራሽ ወደ አራት መቶ ሰው የሚጠጋ ተሰበሰበ፡፡ ሪፖርት አዳመጠ፡፡ አስመራጭ ኮሚቴ መረጠ፡፡ ሰባት አባላት ያሉበት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ ተካሒደ፡፡ አሥራ አራት አባላት ለቦርድ አባልነት ተሰየሙ::

የሥራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት

  1. ኣቶ ኣበረ ምሕረቴ

  2. አቶ ኢሳያስ ተስፋው

  3. አቶ መኮንን ገበየሁ

  4. ዶ/ር አያና የኔአባት

  5. አቶ ጤናው አንዱዓለም

  6. ሲ/ር ለምለም በላይ

  7. አቶ ጌታነህ አንተነህ

የቦርድ አባላት

  1. አቶ አብርሃም ወርቅነህ        8. አቶ መኳንንት እጅጉ

  2. ኣቶ ፀጋ ቁምላቸው              9. አቶ ማኀፀንቱ ፈለቀ

  3. አቶ ስማቸው መኮንን          10. አቶ ሽባባው ወሌ

  4. አቶ አያሌው መለሴ            11. አቶ ጋሼ ሕብስቴ

  5. ዶ/ር አብርሃም አስናቀ         12. አቶ መኮንን ወርቁ

  6. ዶ/ር ባዩ ጫኔ                    13. አቶ ድልነሣ ዘውዴ

     

  7.  Dr Shibabaw Yimenu       14. Ato Getachew Desta

የማኀበሩን ስም  ለመሰየም፣ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብና መመስረቻ ጽሑፍ ለማዘጋጀት የአንድ ወር ጊዜ ወሰደ::

መስከረም 1991፡- መድኃኒት መግዣ  ገንዘብ  ማሰባሰብ ተካሔደ:: ብር59,000 አገኘ ግዥውም ተፈጸመ:: የመድኃኒትና የባለሙያ እገዛ በመያዝ ወደ ተጠቁ ወረዳዎች ተዘመተ፡፡

ጥቅምት 1991፡- ፀረ-ወባ ማኀበር ሕጋዊ ፈቃድ እንዲሰጠው  ለፍትሕ  ሚኒስቴር ጥያቄ ቀረበ፡፡

ሕዳር 1991፡- ዘማች ባለሙያዎች ድል አድርገው  ተመለሱ፡፡

ታህሣሥ-መጋቢት 1991፡- በኣዲስ ኣበባና ከአዲስ አበባ ውጭ  ላሉ ወገንና አገር ወዳድ የሆኑትን የመቀስቀስ ሥራ ተሠራ፡፡

ጥር 2ዐ/1991፡- ፀረ-ወባ ማኀበር ሕጋዊነት አገኘ፡፡

መጋቢት 12/1991፡- በጣሊያን ካልቸራል ኢንስቲትዩት የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ ተሠራ፡፡ ከ525 ሺህ ብር በላይ ተገኘ፡፡

  • የስታር ቢዝነስ ግሩፕ 200,000
  • የናይል ኢንደስትሪያል ግሩፕ 100,000
  • የግዮን ኢንደስትሪያል 100,000
  • የናይልኢንሹራንስ 15,000

ሚያዝያ 1991፡- ከክልል ምክር ቤት፣ ከዞን መስተዳደር፣ ከጤና ቢሮ፣ ከአመዝኮ   ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

ግንቦትና ሰኔ 1991፡- የወረዳ ኮሚቴዎች በከተማ  ኗሪዎች  ምርጫ  ተካሔደ::

ሰኔ 1991፡- 25ዐዐ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በክረምት ጊዜያቸው  ዘመዶቻቸውን እንዲያስተምሩ የሁለት ቀናት ስልጠና በመስጠት በመላ ኢትዮጵያ እንዲሰማሩ ተደረገ፡፡

ሐምሌ 1992:- ወባን ለመከላከል ሊያበቁ ከሚችሉ አማራጮች አንዱ  የአጎበር  መጠቀም ነው:: ይህን በተግባር ለማዋል ቅድሚያ ጥናት ማስፈለጉ የግድ   ነውና በተመረጡ ስምንት ወረዳዎች ማለትም በይልማ ዴንሳ፣ በባህር  ዳር ዙሪያ፣ በቡሬ፣ በጃቢ ጠህናን፣ በደንበጫ፣ በማቻክል፣  በቢቡኝና በሁለት እጁ እነሴ ላይ ተካሔደ፡፡ከያንዳንዱ ወባማ የሆኑ ሁለት ቀበሌዎች ተመርጠው፣ ከያንዳንዱ ቀበሌ ለ25 ሰዎች መጠይቅ   ተዘጋጅቶ ቀረበ፡፡ ከመቶ ዘጠና እጁ ስለ አጎበር የማያውቁ ሲሆን፣    ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆኑት ደግሞ እጅግ ዝቅተኛ ናቸው::

ነሐሴ 1992፡- በዚህ ወር በመስከረም ለሚደረገው ጉባኤ ዝግጅት ተደረገ፡፡  የተከናወኑ ሥራዎችንለመገምገም በየወረዳዎች ጉዞ ተደርጓል፡፡ የፀወማን መዋቅር በአዲስ መልክእንዲደራጅ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት አካሒዶ ረቂቅ ጽሑፍ አቅርቧል፡፡

መስከረም 1993:-  ሁለት የተለያዩ ስብሰባዎች ተካሔደዋል፡፡ አንደኛው  በየሦስት ወሩየሚደረገው በዞን መስተዳድሮች፣ የጤና መምሪያዎችና ኣመዝኮ ተወካዮች የሚካሔደው ነው:: ይህ ስብሰባ በፀወማ ጽ/ቤት የተደረገ ሲሆን፣ ባለፉት ሦስትወራት የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውንና

የማኀበሩን ስም  ለመሰየም፣ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብና መመስረቻ ጽሑፍ ለማዘጋጀት የአንድ ወር ጊዜ ወሰደ::

መስከረም 1991፡- መድኃኒት መግዣ  ገንዘብ  ማሰባሰብ ተካሔደ:: ብር59,000 አገኘ ግዥውም ተፈጸመ:: የመድኃኒትና የባለሙያ እገዛ በመያዝ ወደ ተጠቁ ወረዳዎች ተዘመተ፡፡

ጥቅምት 1991፡- ፀረ-ወባ ማኀበር ሕጋዊ ፈቃድ እንዲሰጠው  ለፍትሕ  ሚኒስቴር ጥያቄ ቀረበ፡፡

ሕዳር 1991፡- ዘማች ባለሙያዎች ድል አድርገው  ተመለሱ፡፡

ታህሣሥ-መጋቢት 1991፡- በኣዲስ ኣበባና ከአዲስ አበባ ውጭ  ላሉ ወገንና አገር ወዳድ የሆኑትን የመቀስቀስ ሥራ ተሠራ፡፡

ጥር 2ዐ/1991፡- ፀረ-ወባ ማኀበር ሕጋዊነት አገኘ፡፡

መጋቢት 12/1991፡- በጣሊያን ካልቸራል ኢንስቲትዩት የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ ተሠራ፡፡ ከ525 ሺህ ብር በላይ ተገኘ፡፡

  • የስታር ቢዝነስ ግሩፕ 200,000
  • የናይል ኢንደስትሪያል ግሩፕ 100,000
  • የግዮን ኢንደስትሪያል 100,000
  • የናይልኢንሹራንስ 15,000

ሚያዝያ 1991፡- ከክልል ምክር ቤት፣ ከዞን መስተዳደር፣ ከጤና ቢሮ፣ ከአመዝኮ   ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

ግንቦትና ሰኔ 1991፡- የወረዳ ኮሚቴዎች በከተማ  ኗሪዎች  ምርጫ  ተካሔደ::

ሰኔ 1991፡- 25ዐዐ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በክረምት ጊዜያቸው  ዘመዶቻቸውን እንዲያስተምሩ የሁለት ቀናት ስልጠና በመስጠት በመላ ኢትዮጵያ እንዲሰማሩ ተደረገ፡፡

ሐምሌ 1992:- ወባን ለመከላከል ሊያበቁ ከሚችሉ አማራጮች አንዱ  የአጎበር  መጠቀም ነው:: ይህን በተግባር ለማዋል ቅድሚያ ጥናት ማስፈለጉ የግድ   ነውና በተመረጡ ስምንት ወረዳዎች ማለትም በይልማ ዴንሳ፣ በባህር  ዳር ዙሪያ፣ በቡሬ፣ በጃቢ ጠህናን፣ በደንበጫ፣ በማቻክል፣  በቢቡኝና በሁለት እጁ እነሴ ላይ ተካሔደ፡፡ከያንዳንዱ ወባማ የሆኑ ሁለት ቀበሌዎች ተመርጠው፣ ከያንዳንዱ ቀበሌ ለ25 ሰዎች መጠይቅ   ተዘጋጅቶ ቀረበ፡፡ ከመቶ ዘጠና እጁ ስለ አጎበር የማያውቁ ሲሆን፣    ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆኑት ደግሞ እጅግ ዝቅተኛ ናቸው::

ነሐሴ 1992፡- በዚህ ወር በመስከረም ለሚደረገው ጉባኤ ዝግጅት ተደረገ፡፡  የተከናወኑ ሥራዎችንለመገምገም በየወረዳዎች ጉዞ ተደርጓል፡፡ የፀወማን መዋቅር በአዲስ መልክእንዲደራጅ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት አካሒዶ ረቂቅ ጽሑፍ አቅርቧል፡፡

መስከረም 1993:-  ሁለት የተለያዩ ስብሰባዎች ተካሔደዋል፡፡ አንደኛው  በየሦስት ወሩየሚደረገው በዞን መስተዳድሮች፣ የጤና መምሪያዎችና ኣመዝኮ ተወካዮች የሚካሔደው ነው:: ይህ ስብሰባ በፀወማ ጽ/ቤት የተደረገ ሲሆን፣ ባለፉት ሦስትወራት የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውንና

 በጋራ ማቀድና መንቀሳቀስውጤቱ የላቀ እንደሚሆን ትምህርት ተገኝቷል፡፡ ሁለተኛው ስብሰባ ደግሞ ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ ያንድ ዓመቱ የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስሪፖርት ቀርቧል፡፡ ማኅበሩ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር ተሻሽሎ የቀረበው መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ፀደቀ፡፡

በዚህም መሠረት:-

ሰባት የቦርድ አባላት እና ሦስት ተጠባባቂ ኣባላት ተመረጡ፡፡ እነሱም

  •  ኣቶ ኣብርሃም ወርቅነህ                            1. ሲ/ር ለምለም በላይ

  • ኣቶ ጌታቸው ደስታ                                  2. ዶ/ር ኣብርሃም ኣስናቀ

  • ኣቶ ኢሳያስ ተስፋው                                3. አቶ ጋሼ ሕብስቴ

  • አቶ መኮንን ገበየሁ

  • ኣቶ ፀጋ ቁምላቸው

  • ዶ/ር ሽባባው ይመኑ

  • አቶ አበረ ምሕረቴ

በዚህ ጉባኤ ላይ የየወረዳ ፀወማ ሰብሳቢዎች እና የየዞኑ መስተዳደር፣ የጤና መምሪያ፣የአመዝኮ እና የጤና ቢሮ ተወካዮች እንዲገኙ በመደረጉ ለጉባኤው ልዩ ድምቀት ሰጥቶታል፡፡በሲድኒ የኦሎምፒክ ማጠቃለያ ዕለት የተካሔደ ስብሰባ ነበር፡፡ አትሌቲክስ በኢትዮጵያ ድልአድራጊነት መጠናቀቁ ለተሳታፊዎች ልዩ ሞራልና የማኅበሩ ድሎች ከኦሎምፒኩ ድል ጋርአብረው እንዲንፀባረቁ ሆኗል::

ጥቅምት1993 ፡- የቦርድ የመጀመሪያ ስብሰባ ተካሔደ፡፡ በፀደቀው መመሥረቻና  መተዳደሪያደንብ መሠረት ቢሮው በሚደራጅበት መንገድ ላይ    ውይይት ተደረገ፡፡ የቢሮናየፕሮጀክቱ በጀት ተጠንቶ እንዲቀርብ ተወሰነ፡፡ አጋር መጽሔት ለየወረ ዳው  ታደለ፡፡

ኅዳር1993፡- ቢሮው  አቶ አበረን በዲሬክተርነት እንዲመሩት ወሰነ::ከቦርድ አባልነት እንዲወጡና በ ሲ/ር ለምለም እንዲተኩ ተደረገ::አንድ ፕሮጀክት ኦፊሰርም እንዲኖረው ተደረገ፡፡ የሦስት ወሩ የዞኖ ችና ፀወማ ስብሰባ በባህር ዳር ልዩጤና መምሪያ ጽ/ቤት ተካሔደ፡፡ የወባ ወረርሽኝ በዳንግላና በአዋበልወረዳዎች ብቻ የተከሰተ ሲሆን ከዳንግላ ሦስት ሰዎች ከመሞታቸው በስተቀርወዲያው በቁጥጥር ስር መዋሉ ተዘግቧል፡፡ ለዚህም የቦታው ርቀትና የመገናኛአለመኖር ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ታይቷል፡፡ ከጥር እስከ የካቲት በሁሉም ወረዳከተሞች ባጠቃላይ 868 የሃይማኖት አባቶች፣ ለ868 እናቶችና ሴቶች ለሁሉም  ት/ቤት ርዕሳነ መምህራን የሁለት ቀናትና የአንድ ቀን ሲምፖዚዬም እንዲካሔድ ተወሰነ፡፡ ፀወማ ውሉ አበል እንዲችል፣ የማስተማሪያ መጽሐፍ አዘጋጅቶእንዲያቀርብ፣ ጤና መምሪያው አስተማሪዎች እንዲመደብ፣ መስተዳደር አዳራሽ  እንዲያዘጋጅና ጥሪ እንዲያስተላልፍ ተወሰነ፡፡ በ21 ወረዳዎች የግምገማ ሥራ ተሠራ፡፡የወባ የአምስት ዓመት ዕቅድ በጤና ጥበቃ አዘጋጅነት በናዝሬትከተማ ለአምስት ቀናት በተካሔደው ስብሰባ ፀወማም ተካፈለ፡፡ በኢትዮጵያውስጥ ለመስራት የሚያስችለውን የ5 ዓመት በጀት ለጤና ጥበቃ አቀረበ፡፡

ለየወረዳ ፀወማ ሁለት ደስታ ወረቀት ለጽሕፈት ሥራ እንዲያገለግል ታደለ፡፡

ታህሳስ1993 :- ቀሩት ሌሎች ወረዳዎች የግምገማ ሥራ ተከናወነ፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና በራዲዮ ፋና አዘጋጅነት በተካሔደው የገና በዓል አከባበር ላይ ከጽ/ቤቱ፣ ከባሶ ሊበንና ከደምበጫ ወረዳ ተደረገ፡፡

ጥር1993፡- በወባ ላይ የማስተማሪያ መጽሐፍ ዝግጅት ተካሔዶ ሕትመቱ ተጠናቀቀ፡፡ ፀወማ የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት አባል ሆነ፡፡ በኤግዚቪሽን ማዕከል በተደረገው ኤግዚቪሽን ላይም ተካፈለ፡፡ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዳራሽ በኤድስ ላይ ለሁለት ቀናት በተካሔደው ሲምፖዚዬም ላይ ተሳተፈ፡፡ በወባ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስና በግልና አካባቢ ንጽሕና ላይ በአዊና በምሥራቅ ጎጃም ዞኖች ለሐይማኖት አባቶች፣ ለእናቶችና ሴቶች? ለርዕሳነ መምህራን የታቀደው ሲምፖዚዬም  ተካሔደ፡፡ በፀወማ የተዘጋጀ መጽሐፍ፣ ከጤና ጥበቃ የተገኙ መጽሔቶችና፣ በራሪ ጽሑፎች በነፃ ታደሉ፡፡ ከጤና አጠባበቅ ማዕከል በተቀዱ ቪዲዮ ካሴቶች ሰፊ ትምህርት በደጀን፣ በአዋበል፣ በዳንግላና በጓንጓ የወረዳ ከተሞች ተሰጠ፡፡

በመስከረም ወር 1993 ዓ.ም:- አዲስ በፀደቀው መዋቅር መሠረት የሥራ አመራር ቦርድ ጥር 5 ቀን 1993 ዓ.ም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉት ግለሰቦች እና ድርጅ ቶች ውስጥ በውጭ አገር ከሚገኙ 4 ፣በአገር ውስጥ ከሚገኙ 7 ግለሰቦችና 2 ድርጅቶችን ለክብር መማክርት አባላት መረጠ፡፡ እነሱም

  • ዶ/ር ይደልዎ አስቡ/ በሳንዲያጎ/
  • ዶ/ር አብርሃም በቀለ /በዋሽንግተን/
  • ዶ/ር ደስታ አላምረው /በቦትስዋና/
  • ኣቶ ድልነሳው ቢተው /በዋሽንግተን/
  • አቶ ወልደሔር ይዘንጋው /በአአ/
  • አቶ ተመስገን መሐሪ /ኣ.አ/
  • አቶ ምንውዬለት አጥናፍ /ኣአ/
  • አቶ አበባው ደስታ /አአ/
  • አቶ ሙሉጌታ አያሌው /አ.አ/
  • አቶ ነጋ ገብረ/እግዚአብሔር /አኣ/
  • እቶ አሥራት መኮንን /አኣ/
  • UNICEF (የተ መ ረ መ ድ)
  • WHO (የዓ ጤ ድ)

የካቲት1993፡- ከዮኒሴፍ አንድ አውቶሞቢል በዕርዳታ ስለተገኘ ቀረጥ በመክፈል ለማኅበሩ አገልግሎት ውሏል፡፡ ያገለገሉ የወንበርና የጠረጴዛ ርዳታዎች ተገኝቷል፡፡ በአሜሪካ በዋሽንግተን የተቋቋመው የተስፋ ማኅበር የገንዘብ ማሰባሰብ አካሒዶ ብር 184,920.12 ለማኅበራችን ልኳል፡፡ ወ/ሪት ኣልማዝ ኣንተነህ በእንግሊዝ ሀገር በለንደን ኗሪ የሆኑ ብር 48,382.08 ለመጽሐፍ ማሳተሚያና ለሲምፖዚዬም እንዲውል ዕርዳታ ሰጡ፡፡ 

መጋቢት1993፡- በባህር ዳር ልዩ ዞንና በምዕ ራብ ጎጃም ዞን ቀጣይ ሲምፖዚዬሞች ተካሔዱ፡፡ ተመሳሳይ ሥራዎችም ተሠሩ፡፡ በአራቱ ዞኖች ሊካሄድ የታቀደው በዚሁ ተጠናቀቀ፡፡ የተገኙ አባላትን ብዛት በገጽ 11 ላይ ይመልከቱ፡፡ የዞንና የፀወማ መደበኛ ስብሰባ በእንጅባራ ተካሔደ፡፡ እንደ ሁልጊዜውም  ያለፉት ሦስት ወራት እንቅስቃሴዎች ተገመገሙ:: ወደፊት የሚከናወኑትም ታቀዱ፡፡ ውጤቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ አበረታች መሆኑ ተሰምሮበታል፡፡ በቀጣይነትም የወረዳ ፀወማ አባላትን፣ የማኅበራዊ ዘርፍንና ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎችን፣ የዞን ማኅበራዊ ዘርፍን፣ ጤና መምሪያና አመዝኮ ኃላፊዎችንና የጤና ቢሮ ተወካይን ያቀፈ የሁለት ቀናት ስብሰባ በደብረ ማርቆስ እንዲካሔድ ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ የፀወማ አባላትን ፀወማ ሊችል የወረዳ መስተዳደርና ጤና ጽ/ቤትን በተመለከተ ራሳቸውን ችለው እንዲመጡ ወይም ደግሞ የሚቻል ከሆነ ሁሉም በየፊናው ገንዘብ እንዲያፈላልግ ውሳኔ ተላለፈ፡፡ በ10/07/93 ዓ.ም ከኔዘርላንድ ብር 3,344,69 ከአንድ ትምህርት ቤት የወላጆች ኮሚቴ ተሰብስቦ ለማኅበራችን ዕርዳታ ተለገሰ፡፡

ግንቦት 1993፡- በደብረ ማርቆሰ ከተማ የ31 ወረዳ የፀረ ወባ ማኅበራት 2ኛ ጉባኤ ተካሄደ፡፡ በጉባኤውም ፀረ-ወባ ማኅበር ባለፉት ሁለት ዓመታት ያከናወናቸውን ሥራዎች ከተወያየባቸው በኋላ ጥንካሬውን ይበልጥ አዳብሮ ከሰኔ 1993 ዓ.ም ጀምሮ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገባቸውን ዕቅዶች አውጥቷል፡፡ የሕብረተሰቡን የግንዛቤ አድማስ ለማስፋትና ራሱን ከወባ፣ ከኤች አይ ቪ ኤድስና ከሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ለመከላከል የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ማሰልጠንና  በዕረፍት ጊዜያቸው ወገናቸውን እንዲያስተምሩ ለማድረግ ተስማምቷል፡፡ የሀይማኖት መሪዎችንና የዕድር አመራር አባላትንም ሕብረተሰባቸውን እንዲያስተምሩ የግንዛቤ አድማሳቸውን የሚያዳብሩበትን መንገድም ቀይሷል፡፡ በዚሁ በግንቦት 4-5 ቀን 1993 ዓ.ም የተሳተፉት አባላት ዝርዝር ከዚህ በታች የሚከተለው ነው፡፡

➢ አምስት ሺህ የአጋር መጽሔት አሳትሞ ለሕብረተሰቡ በነፃ አከፋፍሏል::

ሰኔ እና ሐምሌ 1993፡- በፍኖተሠላም ከተማ የፀረ-ወባ ማኅበር አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ – በግንቦት 4-5 ቀን 1993 ዓ.ም በወረዳ ፀረ-ወባ ማኅበራት ጉባኤ በተወሰነው መሠረት በአራቱ ዞኖች የሚገኙ የ21 ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን የዕውቀት አድማስ ለማዳበርና እራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ሕብረተሰባቸው ከወባና ከኤች አይ ቪ ኤድስ የሚከላከሉበትንና የራሳቸውንና የአካባቢያቸውን ንጽሕና የሚጠብቁበትን ትምህርት በጤና ባለሙያዎች በቪዲዮ ፊልም አጋዥነት ለ18,088 ወጣት ተማሪዎች የአንድ ቀን ትምህርት፤ በዕረፍት ጊዜያቸው ወገናቸውን ለማስተማር በጎ ፈቃደኛ ለሆኑ 3,129 ተማሪዎች ደግሞ የሁለት ቀናት ተጨማሪ ሥልጠና ሰፋ ባለ መንገድ ተሰጥቷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 1,721 ተማሪዎች ከፍተኛ ሥራ ሠርተው የተመለሱ ሲሆን በአማካኝ አንድ ተማሪ 100 ሰው በማስተማሩ በአጠቃላይ ለ172,100 ሰዎች ትምህርቱ ተሰጥቷል፡፡

➢ አምስት ሺህ የወባ በሽታ መነሻና መከላከያው፤ አሥር ሺህ ጥቂት ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ፤ ኣሥር ሺህ በበጎ ፈቃደኛነት የኤች አይ ቪ ኤድስ የደም ምርመራ፤ የሚሉ የማስተማሪ መጽሔቶች አሳትሞ ለሕብረተሰቡ በነፃ አከፋፍሏል፡፡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሥልጠና ተከፋዮች የዘመቱና ሰርተው የተመለሱ::

ነሐሴ 1993፡- የዕድር ኣመራር አባላት፣ የሰንበት፣ የቆሎና የእስልምና ት/ቤት ተማሪዎችንና አስተማሪዎችን ያቀፈ የሁለት ቀን ትምህርት በኤች አይ ቪ፣ በወባና በግልና በአካባቢ ንጽሕና ላይ በ29 ከተሞች ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ ባጠቃላይ 3,919 ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ በዚህ ወቅትም 5 ሺህ በወባ ላይ 20 ሺህ በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ የማስተማሪያ አነስተኛ መጽሐፍ ተሰራጭቷል፡፡ ፀወማ ለሕብረተሰቡ የቆመ ማኅበር መሆኑን የቆሎ ተማሪዎች ከተናገሩት በመጥቀስ ለማሳዬት እንሞክራለን፡፡ “እስከዛሬዋ ቀን ድረስ የመንግሥትም ይሁን የሕዝብ ወይም የግል ድርጅቶች የሕብረተሰብ አካልናችሁ፣ ጠቃሚ ሥራም ትሠራላችሁ ብሎ ያሰበና የጠራን ድርጅት ከፀረ-ወባ ማኅበር በስተቀር የለም”::

መስከረም 1994፡- ቪዲዮ ፕሮጀክተር በመግዛትና ከ’ኤድስ መከላከያና ማኅበራዊ ኣገልግሎት ድርጅት” በመዋስ ጄነሬተርና ስክሪን በመግዛት በገጠር ከተሞች በኤች አይ ቪ ኤድስ፣ በወባና በግልና አካባቢ ንጽሕና ላይ ቅስቀሳ ማካሔድ ተጀምረ፡፡ እስከ ታህሳስ ወር ድረስ በ60 ቦታዎች ለ66,680 ሰዎች አሳይተናል፡፡

ጥቅምት 1994፡- በመጀመሪያ ከ21 ት/ቤት የዘመቱ ተማሪዎች የሠሩትን ሥራና ባጋጠማቸው ችግር ላይ በት/ቤት ደረጃ እንዲወያዩ ተደረገ፡፡ ሰርተፊኬት ታደለ፡፡ ብልጫ ያሳዩ 20 ተማሪዎችም ከእያንዳንዱ ት/ቤት እንዲመረጡ ተደረገ፡፡ የተመረጡ ተማሪዎች ከርዕሰ መምህራንና ፀወማ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ከወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በባህር ዳር የአንድ ቀን ስብሰባ ተካሔዶ ሰፊ ውይይት ተደረገ፡፡ ለቀጣዩም ክረምት ተመሳሳይ ዕርምጃ ለመውስድ ስምምነት ላይ ተደርሶ ሁሉም አንድ አንድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ተሸለሙ፡፡

ኅዳርና ታህሳስ 1994፡- ሦስት ግዙፍ ሥራዎች ተሠሩ፡፡ አንደኛው ከ920 ቀበሌ የተውጣጡ ሁለት ሁለት የቀበሌ ፀወማ ኮሚቴ አባላት በ29 ከተሞች የሁለት ቀናት ትምህርት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ባጠቃላይም 1,588 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም 270 ለሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከቤት ቤት እየተዘዋወሩ ትምህርት እንዲሰጡ የሚያስችል የሁለት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷቸው እንቅስቃሴ ጀመሩ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ከ300 ሺህ ሕዝብ በላይ ለማስተማር ተችሏል፡፡ ሦስተኛው ደግሞ በስዊድን አገር ኗሪ ከሆኑ ከአቶ አዳሙ አንለይ ጋር በተደረገ ስምምነት ለፍኖተ ሠላም ሆሰፒታልና ለፈረስ ቤት ጤና ጣቢያ የሚያገለገሉ የህክምና መርጃዎችን ከቀረጥ ነፃ በማስገባት እርዳታው እንዲደርስ አድርገናል፡፡ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የካቲት 1994፡- ሁለት ትላልቅ ስብሰባዎች ተከናወኑ፡፡ አንደኛው የወረዳ የፀረ-ወባ ማኅበር ኮሚቴ አባላትን ያቀፈ የሁለት ቀናት ስብሰባ የካቲት 18 እና 19 በባህር ዳር፣ በእንጅባራ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በደብረ ማርቆስና በቢቸና የተካሔደ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የካቲት 30 ቀን በደብረ ማርቆስ ከተማ የ33 ወረዳ አሰተዳዳሪዎችን የ33 ወረ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የ32 ወረዳ ፀወማ ኮሚቴ አባላትን፣ የአራቱ ዞን አስተዳዳሪዎች፣ የአራቱ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊዎች የ3ዞን አመዝኮ ኃላፊዎች የጤና ቢሮ፣ የኤች አይ ቪ ሴክሬታሪያት፣ የአመዝኮ ኃላፊ ወይም ተወካዩትና የፀወማ ተወካዮች የተገኙበት ስብሰባ ነው፡፡ የሁለቱም ስብሰባ ዓላማዎች ያለፉትን የፀወማ እንቅስቃሴዎች መገምገምና ወደፊት መደረግ ስላለባቸው ሥራዎች መወያዬት ነበር፡፡ የመጀመሪያው ስብሰባ ለሁለተኛው ቀርቦ ውይይት ተካሔደበት፡፡ በአንድ ቃልም ማኅበሩን ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡ አባል በመሆን፣ የወረዳ ፀወማ ቢሮዎችን በማደራጀት የተዳከሙ ኮሚቴዎችን በማጠናከር፣ ሪፖርቶች በወቅቱ ለማስተላለፍ ጥረት ለማድረግ ስምምነት ተደርጎ ተፈጽሟል፡፡

መጋቢት 1994፡- የፓርትነርስ ኢን ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ዲሬክተር ሚስተር ጆን ቤንጀት የተባሉ ካናዳዊ ከማኀበራችን ጋር አብረው ለመሥራት በመፈለጋቸው ሃያ አራት ወረዳዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡ የመጀ መሪያ ምርጫቸውም በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ለመሥራት ስለሆነ በሞጣና በመርዓዊ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የመፀዳጃ ቤቶች* ለመሥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝም ፀረ-ወባ ማኀበር መፀዳጃ ቤቶች እየሞሉ ከመደፈን እንዲድኑ ተጨማሪ ወጪ በማውጣት የባዮ ጋዝንና የባዮ ፋርምን አጠቃቀም ለማስተማር እንዲቻል ኘሮጀክት ነድፏል፡፡ የፀረ-ወባ ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሔደ፡፡ የሥራ እንቅስቃሴዎች እድገት ተደንቀው በርቱ ተበራቱ የሚል ድጋፍ አገኘ፡፡

ሚያዝያ 1994፡- የአገር አቀፍ ፀረ-ወባ ማኀበር የተወሰኑ ወረዳዎችን ጐበኘ፡፡ የወባ ወረርሽኝ አደጋ እንዳለ ጠቆመ፡፡ አግባብነት ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመወያየት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ ማሳሰቢያ ሰጠ፡፡ በፊልም የተደገፈ ቀስቃሽ ትምህርት አሳሳቢ ናቸው በተባሉ ቦታዎች እንዲሰጥ ተደረገ፡፡ የዞን ፀወማ ተወካዮች በየወረዳዎች በመሔድ የወባ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል የወረዳ መስተዳደር የጤና ጽ/ቤትና የፀወማ ኮሚቴ በአንድ ላይ በመሰብሰብ በቅንጅት ቅድሚያ መከላከል ሥራ እንዲሠራ ማሳሰቢያ ሰጡ፡፡ በዓለም አቀፍ ጤና ተቋም የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ዲሬክተር ዶ/ር ጃንክሎስ ሚሼል አዴት፣ ባህርዳርን፣ መርዓዊንና በሜጫ ወረዳ የሊም ቀበሌንና ዱርቤቴን እንዲጐበኙ ተደረገ፡፡የተቆፈሩ መፀዳጃ ቤቶችንና በዱር ቤቴና በባህር ዳር የማኀበሩን ጽ/ቤት ጎብኝተዋል፡፡ አዲስ አበባ ሲነገራቸው ማመን ተቸግረው እንደ ነበረና በጉብኝታቸው ያዩት ግን ከተነገረው የበለጠ እንደሆነ 

በጉብኝታቸው ወቅት ከመንግስት ጋር ያለን ቅንጅት፣ ከጤና ቢሮ ጋር ያለን ትብብርና ከኀብረተሰቡ ጋር ያለንን ውሕደትና የተሠሩ ሥራዎችን እንዲጐበኙ ተደርጓል፡፡ በዚህ ጉብኝታቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዘማች ተማሪዎች በአዴት የተደራጁ 89 ሴተኛ አዳሪዎችን፣ በሊም ቀበሌ መስክረዋል፡፡ ሁለት ኘሮጀክቶች ባስቸኳይ እንዲሰሩ ረዳት ሰጥተው በራሳቸው አባሪ ደብዳቤ ለተለያዩ አገሮች ልከዋል፡፡ የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት አንድ ፕሮጀክት ኦፊሰር የደመዋዙን 75% በመቻል ቀጠረልን፡፡ ኣንድ አነሰተኛ ካነን ማባዣ ገዝቶ አበረከተልን፡፡

ግንቦት 1994፡- የወባ ወረርሽኝ በአቸፈር፣ በጓንጓና በጃቢ ጠህናን የከፋ እየሆነ መጣ፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት ለተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ለማሳወቅ ጥረት ተደረገ፡፡ ለጃቢ ጠህናንና ለጓንጓ ወረዳዎች ፀወማ ባለሙያዎች በመላክ ዕርዳታ እንዲሰጡ አደረገ፡፡ ባለሙያዎችን በሚቀርብልን የስልክ ጥሪ መሠረት ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ጥድፊያ የሞላበት ዘመቻ ኣከናወኑ፡፡ ወረርሽኙን በማርገብ ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ፡፡ለስዊድን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅትና ለሴክሬታሪያት የተለያዩ ኘሮጀክቶች አቀረብን፡፡

ሰኔ 1994፡- የወባ ወረርሽኝ የቀጠለ ቢሆንም ረገብ ማለት ጀምሯል፡፡ ባለሙያዎች ተመልሰዋል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ስልጠና እንዲወስዱና አስፈላጊውን የማስተማሪያ ትጥቅ እንዲያገኙ ተደርጐ ዘመቱ፡፡ በጐ ፈቃደኞች በዓለም አቀፍ የወባ ስብሰባ በኢንቴቤ እንድንገኝ ባደረግነው ጥረት ተሳክቶልን የክልል ወኪላችን ዶ/ር መኮንን አይችሉህም ለአንድ ሳምንት ተሳትፈው ተመለሱ፡፡

ሐምሌ 1994፡- የኦዲት ዝግጅት ተደረገ፡፡ ዓመታዊ የቋሚ ንብረት ቆጠራ ተከናወነ፡፡ ከስዊድን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅትና ከኤች አይ ቪ ሴክሬታሪያት ጋር የሦስት የሦስት ፕሮጀክቶች ሥራ ስምምነት ውል ተፈራረምን፡፡

ነሐሴ 1994፡- የጋራ ስብሰባ በደብረ ማርቆስ ተካሔደ፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ወረዳ ኣስተዳዳሪዎች፣ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ወረዳ ፀ.ወ.ማ. ሰብሳቢዎችና የጤና ቢሮ ተወካዮች፣ የኤች አይ ቪ ሴክሬታሪያት ኃላፊ የዞን ሴክሬታሪያት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡ በፀ.ወ.ማ. የወባ ወረርሽኝ ሊከሰት ስለሚችል ያላሰለሰ ጥረት እንዲደረግ ማሳሰቢያ ቀርቦ በመድኃኒት በኩል ችግር አለመኖሩ፣ ከጤና ቢሮና ዴስክ ተገልጾ ፀረ-ወባ ማኀበር የወረርሽኝ ጥቆማ የሚያደርጉ፣ ትምህርት የሚሰጡና ኅብረተሰቡን በመቀስቀስ የአካባቢ ቁጥጥር እንዲሠራና የታመሙት ባስቸኳይ ወደ ጤና ጣቢያ ወይም ክሊኒክ እንዲሔዱ የማድረግ ሥራ እንዲሠራ ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በኤች አይ ቪ ዙሪያም በቅንጅት በመሥራት ዓይነተኛ ሚና እንድንጫወት የጋራ ግንዛቤ ላይ ተደረሰ፡፡ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ 197 ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴቶችንና ከምሥራቅ ጐጃም ወረዳዎች 87 አቻ ላቻ አስተማሪዎች ከኤች አይ ቪ ሴክሬታሪያት ባገኘው ገንዘብ፣ 18ዐ አቻ ላቻ አስተማሪዎች ደግሞ ከምዕራብ ጐጃም፣ ከአዊና ከባህር ዳር ዞኖች 18 ወረዳዎች ከስዊድን ተራድኦ ድርጅት በተገኘ ገንዘብ በባህር ዳር፣ በዳንግላ፣ በእንጅባራ፣ በቡሬ፣ በደምበጫ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በብቸናና በሞጣ ከተማ በወባ፣ በኤች አይ ቪና በአካባቢና የግል ንጽሕና ላይ የ3 ቀናት ሥልጠና አግኝተው ዘመቱ፡፡ የወባ ወረርሽኝ በከፋ መልኩ በአገራችን ሊከሰት እንደሚችል በጽ/ቤታችን ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡ ቀጥሎም በአቸፈር፣ በሜጫና በጐንቻ ሲሶ እነሴ ወረርሽኝ መነሳቱንና ዕርዳታ ማድረግ የሚፈልግ ወደ ማኀበራችን ጽ/ቤት በመምጣት መሳተፍ እንደሚችል በድጋሚ በሚዲያ አሳወቅን፡፡

መስከረም 1995፡- የወባ ወረርሽኙ እየከፋ ለመጣባቸው ለአቸፈር፣ ለሜጫና ለባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ የመድ ኃኒት አቅርቦት እንዲኖር ጥረት ተደረገ፡፡ ከጤና ቢሮው ጋር ውይይት በማድረግ ድጋፉ ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡ ሆኖም ችግሩ እየተባባሰ በአቸፈር 19 ቀበሌዎችን በሜጫ 24 ቀበሌዎችን አዳረሰ፡፡ “የሮል ባክ ማላሪያ” የአገር አቀፍ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡ ማኀበራችን የሥራውን ሪፖርት አቀረበ፡፡ በሁሉም ተሰብሳቢዎች በኩል ሰፊ ድጋፍ አግኝቷል፡፡ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴቶችና አቻ ላቻ ዘማቾች በሠለጠኑባቸው ስምንት ከተሞች ተገናኝተው በሠሯቸው ሥራዎችና ባጋጠሟቸው ችግሮች ላይ ተወያይ ተዋል፡፡ የወባ ወረርሽኝን ችግር አስታውቀዋል፡፡ በክረምት ዘምተው ሥራ ሠርተው የተመለሱ የ22ም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች ደረጃ ወጣ፡፡ የሠርተፊኬት ሽልማት በየት/ቤቱ ተሰጠ፡፡ አቶ መስፍን ተክሉ የተባሉ በጎ አድራጊ አንድ ኮምፒውተር በዕርዳታ አበረከቱ፡፡

ጥቅምት 1995፡- በቡሬ፣ በጃቢ ጠህናን፣ በደምበጫ፣ በቋሪት፣ በሸበል በረንታ፣ በቢቡኝ፣ በጐንቻ ሲሶ እነሴ፣ በጐዛምን፣ በማቻክልና በሁለት እጁ እነሴ ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ አድማሱን በማስፋት ሰፊ ቦታዎችን አዳረሰ፡፡ ከጤና ቢሮው ጋር በቅንጅት ሥራዎቻችን ላይ ውይይት አካሒደናል፡፡ በየሦስት ወሩ ተገናኝተን ለመወያየት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ በባህር ዳር ከተማ ከ22 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከእያንዳንዱ ት/ቤት በተመረጡ ሃያ ሃያ ተማሪዎች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ የወረዳ ፀ.ወ.ማ. ሰብሳቢዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአጠቃላይ ከ515 ተሳታፊ ዎች ጋር የሁለት ቀናት ስብሰባ አካሂደናል፡፡ በሠሯቸው ሥራዎች፣ በታዩ ለውጦችና ባጋጠሟቸው ችግሮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ኣንዳንድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላትና አንዳንድ ሐኪም በሌለበት የሚል መጽሐፍ እንዲሸለሙ ተደርጓል፡፡ ጭስ አባይንም ጐብኝተዋል፡፡ ወጪውን በመሸፈን ከፍተኛ ድጋፍ ያደረገልንን የስዊድን ተራድኦ ድርጅትን ማመስገን እንወዳለን፡፡ የወባ ወረርሽኝን ችግር ለመቋቋም የተጠናከረ ሥራ እንዲሠራ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል፡፡ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴቶችና አቻ ላቻ ዘማቾች ወርሃዊ ስብሰባ በስምንቱ ከተሞች ተካሔደ፡፡ በሁሉም 22 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተጨማሪ ሰላሳ ሰላሳ በጎ ፈቃደኛ ዘማቾች የመጽሐፍ ሽልማት ተሰጠ፡፡ የሥነ-ጽሑፍ ውድድር በሁሉም 22 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተካሂዶ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ከ1ኛ እስከ 5ኛ ለወጡ 110 አሸናፊ ተማሪዎች የመጽሐፍት ሽልማት ተሰጠ፡፡ ፕሮጀክቱ የተከናወነው በዓለም አቀፍ የኤድስ ቢሮ ድጋፍ ነው፡፡ ከተለያዩ ግለሰቦች ሁለት ኮምፒውተሮች በዕርዳታ ኣገኘን፡፡

ኅዳር 1995:- በደብረ ማርቆስ ከተማ የወረዳ ፀወማ ሰብሳቢዎች፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች የጤና ቢሮ ተወካዮች፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና ኃላፊዎች በአጠቃላይ 105 አባላት ያሉበት የሩብ ዓመታዊ ውይይት ተካሄደ፡፡ በወባ ወረርሽኝ ዙሪያም   

ሰፊ ውይይት ተደርጎ እርምት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ስምምነት ላይ ተደርሶ የፀረ-ወባ  ማኅበር በዕለቱ የ77,000 የፋንሲደርና የ50,000 ክሎሮኪን ክኒን አስረከበ፡፡ በደምበጫ፣ በጃቢ ጠህናን፣ በባህር ዳርና በደብረ ማርቆስ ወረዳዎች የጤና ባለሙያዎች በማዝመት ድጋፍ አድርጓል፡፡ የአቻ ለአቻና፣ የወጣት ሴቶች ወርሃዊ ስብሰባ በስምንቱም ከተሞች በወሩ የሠሩትን ሥራ ተወያይተው የሚቀጥለውን ወር ሥራ ነድፈዋል፡፡ የአቻ ለአቻና የወጣት ሴቶች ባደረጉት ውይይት ፀወማ ከሚከፍላቸው ወርሃዊ የትራንስፖርት አበላቸውን 40% በአራት ወራት ተቀናሽ ተደርጎ ግማሹን ማኅበሩ የወባ መድኃኒት እንዲገዛበት ግማሹን ደግሞ ለድርቅ ለተጎዳው ወገኖቻችን ይሰጥልን በማለት ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ የማኅበሩ የፅሕፈት ቤት ሠራተኞችም ከወር ገቢያቸው 25% ለተመሳሳይ ዓላማ አዋጡ፡፡ በአጠቃላይ ብር 20,982.50 ተሰበሰበ፡፡ የመፀዳጃ ቤቶች የግንባታ ሥራ በሞጣና በመርአዊ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፓርትነርስ ኢን ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ በተገኘ ድጋፍ ተጀመረ፡፡

ታህሳስ 1995፡- ማኅበሩ ባለፈው ወር በተዋጣው ገንዘብ በብር 10,474.38 የወባ መድኃኒት ገዝቶ ለክልሉ ጤና ቢሮ ሲያስረክብ ብር 10,491.25 ደግሞ ለክልሉ ኣመዝኮ አስረክቧል፡፡ የ1994 ዓ.ም የበጀት ዓመት ኦዲት ሪፖርት ተጠናቀቀ፡፡ ከቴክሳስ ጎልማ ጋር ሰባት ወላጅ አልባ ሕፃናትን ለመርዳትና ለማስተማር ስምምነት ተፈረመ፡፡ የአቻ ላቻና ትምህርታቸውን ያቋረጡ ወጣት ሴቶች ወርኃዊ የሥራ ውይይት በስምንቱም ከተሞች ተከናወነ፡፡ ከክልል ጤና ቢሮ ጋር የሩብ ዓመት የሥራ ሂደት ውይይት ተደረገ፡፡ የየወረዳ ፀወማ ኮሚቴዎች በአባላት የተመረጡ አዲስ ኮሚቴ አዋቅረው እስከ የካቲት 30 ቀን 1995 ዓ.ም እንዲያሳውቁ መመሪያ ተላለፈ፡፡ አቶ ኤርሚያስ መብራቴ መንግሥቴ የተባሉ በጎ ፈቃደኛ ከአሜሪካ የዕረፍት ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ የአንድ ሳምንት ለጽ/ቤታችን ሠራተኞች የኮምፒተር ሥልጠና ሰጡ፡፡

ጥር 1995፡- ከአማራ ኤች አይ ቪ ኤድስ ሴክሬታሪያት ጋር የተደረገው የሦስት ፕሮጀክቶች ሥራ በመጠናቀቁ ሂሳቡን ያለእንከን አወራርደን ዘግተናል፡፡ በፍኖተ ሰላምና በዳንግላ ከተሞች በየወረዳው ገንዘብ በሚያዋጡ አባላት የኮሚቴ  ምርጫ ደረገ፡፡ ሚስስ ጆርዲና ሐምፍሬይስ የተባሉ እንግሊዛዊት ለዕረፍት ሲመጡ በባህር ዳር ጽ/ቤት ነፃ አገልገሎት ሥራ በፕሮጀክት ላይ ለመስጠት ማኅበራችንን ተቀላቀሉ፡፡

የካቲት 1995፡- በየዕድ ውሃ፣ በዱር ቤቴና በግምጃ ቤት ከተሞች ገንዘብ በሚያዋጡ አባላት የአዲስ ኮሚቴ ማዋቀር ሥራ ተከናወነ፡፡ ከዋናው ጽ/ቤት የአቻ ለአቻ ዘማቾችን ሥራ በየወረዳው በመዞር ግምገማ አካሔዱ፡፡

Mulu Yeneabat; the first Employee of HDAMA who has served in many positions at a time: project coordinator, communication officer,  project designer, accountant… He had a very good heart for the community. He did not have any reservation for his contribution. He was one of those who put their foot print in the sustainability of the Association..   and who has been a cornerstone for the Association.