
አብጠው ከበደ
ከሸበል በረንታ ወረዳ - አባል
በሃገራችን ለ2ኛ ግዜ የተከሰተውን የወባ ወረርሽኝ በተለይም በአማራ ክልል ከ1990-1995 ዓ.ም በተከሰተው ከፍተኛ ወረርሽኝ ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የህዝብ ባለውለታ የሆኑት የክልላችን ተወላጆች በአንዲት የግል ጋራዥ ውስጥ በነሃሴ 7 ቀን 1990 ዓ.ም የተመሰረተው አገር በቀል ማህበር ከተቋቋመበት ግዜና ወቅት ጀምሮ ለወገን ደራሽ ወገን ነው በጋራ ለውጥ እናምጣ የሚል መሪ ቃል በማንገብ
-
የወባ ወረርሽኝ
-
የኤች አይ ቪ ኤድስን
-
የግልና የአካባቢ ንፅህናን
-
የስነ-ተዋልዶን
-
የአየር ንብረቶችን
በሚሉት ነጥቦች የህዝብ ችግሮችን ለመቆጣጠር ብሎም ለመከላከል በአምስቱ ዋና ዋና የህብረተሰብ ችግሮች መነሻ በማድረግ ለህብረተሰቡ የሚጠቅሙ ስራዎችን መነሻ በማድረግ ለህብረተሰቡ የሚጠቅሙ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ እከናወነም ይገኛል፡፡ በተለይም የወባ ወረርሽኝ በወረዳችን ህብረተሰብ ዘንድ ወባ ዛር ነው፤የእናት የአባት አምላክ ቆሌ ነው እያለ ለብዙ ዘመናት ሲሞኝበትና ሲጎዳበት የነበረውን ባዶ እምነት መሆኑን ለህብረተሰቡ በማስተማርና የወባ በሽታ ዛር ሳይሆን በሽታው የሚከሰተው በትንሽ ነፍሳት የወባ ትንኝ ንክሻ ፕላዝሞድየም በሚባል ተህዋሲ ከበሽተኛ ወደ ጤነኛ ሰው የሚተላለፍ መሆኑን ያሳወቀና የህዝብ ባለውለታ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረ ማህበር ለመሆን በቅቷል፡፡ ሆኖም ግን በሽታውን በአካባቢ ቁጥጥር ስራ መከላከል እንደሚቻልም አስገንዝቧል፡፡
ኤች አይ ቪ ኤድስን በተመለከተም ማህበሩ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ በሽታም ሆነ በሌሎች በሽታዎች ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህጻናትን ወንዶቹ ከብት አቋሚ፤ ሴቶቹ ልጅ አዛይ ሆነው እንዳይቀሩ በማሰብ
-
ወንድ 2 ሴት 4 ድምር 6 ልጆችን በማሳደግና በማስተማር
-
ዲግሪ 2 ዲፕሎማ 4 በማስመረቅ ስራ እንዲይዙ ማድረግ ችሏል፡፡ በሌላ መልኩ በደምብ ልብስና በ/ጽ ቤ/ት እጦት ከት/ም ገበታቸው ላይ እንዳይፈናቀሉ ወንድ 198፣ሴት 274፣ድምር 472 ለሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ አድርጓል እያደረገም ይገኛል፡፡ አሁንም ማህበሩ 10ኛ ክፍል ወንድ 2 ሴት 3 ድምር 5 ተማሪዎችን እያስተማረ ሲሆን 1 ተማሪ በዲግሪ በዚህ ዓመት እናስመርቃለን፡፡ በሌላ መልኩ ኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ለሚኖሩና መገለል ለደረሰባቸው 36 ሰዎች የህክምና ድጋፍ እንዲደረግላቸው አስፈላጊውን ክፍያ በመፈጸም እንዲታከሙ አድርገናል፡፡ እያደረግንም እንገኛለን በመጨረሻም ይህ ማህበር ከአነሳሱ ጀምሮ ከአነሳሱ ጀምሮ ለወገን ደራሽ ወገን ነው በጋራ ለውጥ እናምጣ በሚል መሪ ቃል የተቋቋመ በመሆኑ ከዚህ በላይ እጅግ በጣም በአጭሩ የገለጽናቸውስራዎችን የሰራናቸው በበጎ ፍቃደኞች ሲሆን ማህበሩ በስሩ በአባልነት ካሰባሰብናቸው አባላቱ በመጀመሪያ 0.50 ሳንቲም ከዚያ ቀጥሎ 1 ብር በአሁኑ ሰዓት 2 ብር በወር በማሰባሰብ ሲሆን ይቺን ገንዘብም ለማሰባሰብ የሰው ፊት እሳቱ ጠባሳ አያረግም እንደመፋጀቱ የሚለውን አባባል በመቋቋም ነው እየሰራን ያለነው በተለይም በዚህ በሽታ ሜዳ ላይ የቀሩ ህጻናትን ወደ ህብረተሰቡ ገባ ብለን ለማየት ብንችል እናትም አባትም አልቀው በአንድ ቤት ውስጥ ትንሹ ቁጥር ከ 2-3 ለጆች ትልቁ ደግሞ ስምንት ልጆች እድለኛ የሆኑት አያት ያላቸው ሲሆኑ አብዛኞቹ ግን በአቋጣሪ በሆነ ዘመድ አዝማድ ላይ ፈሰው የሚገኙ ናቸው፡፡ ስለሆነም ወደፊት ይህ ጥሪ የሚደርሳችሁ ሁሉ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን በመረዳት በባንክ ቁጥራችን 1000085663098 በሆነው አድራሻችን ብትደግፉን በታማኝነት ከዚህ በበለጠ ለወገናችን የምንሰራ መሆናችንን ስንገልጽላችሁ በምረዳቸው ህጻናት ስም መሆኑን እንገልጻለን፡፡