HDAMA

ምንውዬለት አስረስ

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር(HDAMA)

ስለ ሰው ልጅ ጤና ስናስብ ወይም ስናነሳ የሰውን ልጅ ጤና ሰለሚያቃዉሱት በሽታዎችና ድንገተኛ አደጋዎች በአንፃራዊነተ ማንሳታችን ወይም ማሰባችን አይቀሬ ነዉ ፡፡

እነዚህም በሽታዎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሲሆኑ ከነዚህም ቀደምቶች ከሆኑት ተላላፊ በሽታች መካከል አንዱ የወባ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ ሞቃታማ የአየር ጸባይ ባላቸው የአለም አገሮች አገራችንን ጨምሮ ዓመቱን በሙሉ በቋሚነት (endemic) አንዳዴም በወረርሽኝ መልከ (epidemic) እየተከሰተ ብዙ የሰዉ ልጆችን በማመም ለስቃይና ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ ነው፡

ይህ በሽታ በአሰተላላፊ ትንኞች አሰተላላፊነት ብቻ በቀላሉ ከበሽተኛ ሰዉ ወደ ጤናማ ሰዉ የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ለበሽታው መዛመትና በወረርሽኝ መልከ መከሰት ዋናዉን ሚና የሚጫወቱት እነዚህ ትንኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ትንኞች በብዛት ከተራቡና በአካባቢዉ የበሽታ አምጭ ህዋስ በደማቸዉ ዉሰጥ ያሉ የተወሰነ ሰዎች ካሉ በሽታዉ በቀላሉ በወረርሽኝ መልከ ይከሰትና ብዙ ሰው ሊታመም ሊሰቃይ ለሞትም ሊዳረማ ይችላል፡፡

እነዚህ ትንኞች በአንድ አካባቢ ለመኖርና ለመራባት እንዲችሉ ሞቃታማ የአየር ፀባይና ያቅረ ንጹህ ዉሃ ሊኖር ይገባል ፡፡ ይህ ምቹ ሁኔታም በአብዛኛው የሚፈጠረው በተለይ በሀገራችን የክረምት ወቅት ሲገባና ሲወጣ ከመጋቢት እስከ ሰኔ ወራቶችና ከመስከረም እስከ ህዳር ወሮች ባሉት ጊዚያቶች ለትንኞች መራባት ምቹ ወቅቶች ሰለሆኑ በአብዛኞዉ በእነዚህ ወቅትች ነው በሽታዉ በወረርሽኝ መልከ የሚከሰተዉ፡፡

በሀገራችን በእነዚህ ወቅቶች በተለያዩ ዓመታት ወረርሽኙ ተከስቷል ፡፡በተለይ 1990/1991 ዓ/ም በሀገራችን የተለያዩ ከልሎች በተለይ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ተከስቶ የነበረዉ ወረርሽኝ ግን በጣም የከፋ ሰለነበር ብዙ ዜጎችን ለህመም ለሰቃይና ለህልፈት ዳርጓል፡፡

ይህኔ ነዉ ፀረ ወባ ማህበር የአሁኑ ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር የተመሰረተዉ ፡፡ይህ ማህበር የተመሰረተዉ ማህበሩ ከተመሰረተበት ጌዜ ጀምሮ እሰከዚህ ዓመት ድረስ የማህበሩ ዳይሬከተር በመሆን የሚያገለማሉት የአተ አበረ ምህረቴ ባለቤት አነሳሽነትና በራሳቸዉ በአቶ አበረ ምህረቴ ተነሳሽነት ሌሎች ጓደኞቻችዉን አነሳሰተዉ በበጎ ፈቃደኝነት ተሰብስበዉ በጋራ በመወያየት ማህበር መስርተው ማህበሩንም ፀረ ወባ ማህበር ብለዉ ሰይመዉ ህጋዊ ፈቃድ አውጥተው አመራር አባላትንም መርጠው በዳይሬከተርነት አቶ አበረ ምህረቴን ሰይመዉ የሰራ ዕቅድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ከየግል ኪሳቸው ገንዘብ አዋጥተው ከሌሎች ለምነው ባሰባሰቡት ገንዘብ የወባ በሽታን የሚፈዉሰን መድሃኒት ገዝተው መኪና ተከራይተው ወረርሽኙ ወደ ከፋባቸው ወረዳዎች በመሄድ ከመንግሰት የጤና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ወደ በሽተኞች ቤት ለቤት በመንቅሳቅሰ መድሃኒቱን ለበሽተኞች በማደል ብዙ በሽተኞች እንዲፈወሱ አድርገዋል።

ማህበሩ ይህን የበጎ አድራጎት ሰራ ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መርህ እየተንቀሳቀሰ የማህበሩንም መዋቅር እሰከ ቀበሌ ድረሰ በመዘርጋት ሰራዉን ሲሰራ ከቆየ በኃላ ወረርሽኙ ጋብ ካለ በኃላና ከተቋቋመበት አላማዉ ጎን ለጎን በሌሎች ማህበራዊ የጤና ችግሮች ላይ ለምሳሌ ኤች አይ ቪ ኤድሰ በመከላከል የንጹህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦትን ወላጆቻቸዉን በተለያየ ምከንያት ያጡ ህጻናትንና ወጣቶችን እየረዳ ማሰተማርን የአካባቢ የአየር ንብረት ጥበቃን የአካባቢ ጽዳትንና የግል ንጽህናን በመጠበቅ ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል መቻልን በተመለከተም የተለያዩ ሰራዎችን ሰርቷል በመሰራተም ላይም ይገኛል፡፡

ይህ ማህበር መንግስታዊ ያልሆነ አገር በቀል ግብረ ስናይ ድርጅት ሲሆን በበጎ ፈቃደኛ አባላቱ አስተዋጽዖና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ግብረ ስናይ ድርጅቶች በሚያደርጉለት ድጋፍ እየተንቀሳቀሰ ብዙ ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታት ላይ የሚገኝ ማህበር ነው።

ይህ ማህበር በተለይ በተለያዩ የጤና ችግሮች ወላጆቻቸውን ያጡና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር የገጠማቸውን ሴት ተማሪዎችን ከከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከሚማሩ ተማሪዎች አወዳድሮ ድሀና ጎበዝ የሆኑ ሴት ተማሪዎችን በመመልመል በደ/ማርቆስ ከተማ ራሱ ባስገነባዉ ህንፃ በአዳሪ ተማሪነት ሁሉንም ወጭዎች ችሎ እየረዳ በማስተማር በተጨማሪም ከወላጆቻቸዉ ጋር ያሉ ድሀ ተማሪዎችን የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ የሚያስተምራቸዉ ተማሪዎች ብዙ ናቸዉ፡፡ማህበሩ ባደረገላቸው ድጋፍ ትምህርታቸዉን አስከ ዩንቨርሲቲ ድረስ ተምረው በዶክትሬት በመሀንዲስነት በሌሎችም የጤና ዘርፎችና በተለያዩ ሙያዎች ተመርቀው ወገናቸዉን ሀገራቸውን እራሳቸውን በማገልገልና በመርዳት ላይ የሚገኙ ብዙ ወጣቶች ናቸው ፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ራሱን ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እንዲጠብቀ የበሽታውን መተላለፊያ መንገዶችና የመከላከያ ዘዴዎችን በተለያዩ ማስ ሚዲያዎች ህትመትና ገጽ ለገጽም ህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስጨበጥ ያደረገወና በማድረግ ላይ ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ሲሆን በንጹህ የመጠጥ ውሃ እጦት ምከንያት የሚከሰቱ አና የሚተላለፉ ዉህ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከል እንዲቻል ጥልቀ የመጠጥ ዉህ ጉድጓዶችን በማስቆፈር ህብረተሰቡ ንጹህ የመጠጥ ውህ እንዲያገኝ በማድረግና በተለይ በገጠር ኗሪ እናቶች የመጠጥ ዉህ ለማግኘት በእግራቸው እስከ አንድ ስዓት ድረስ እንስራ ተሽክመው እየተጓዙ የሚገጥማቸውን ድካም ለማቃለል በየአካባቢያቸዉ ተሰባስበዉ በሚኖሩበት አካባቢ ጥልቀ የውህ ጉድጓድ በማስቆፈር በቀርብ ርቀት ከመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ የመጠጥ ውህ እንዲያገኙ ያደረገና እያደረገ ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው ፡፡

እንዲሁም ደማም በክረምት ወቀት አንዳንድ ወንዞች በጎርፍ አማካኝነት ሲሞሉና በእነዚህ ወንዞች አካበቢ የሚኖሩ ህዝቦች ወንዞችን ተሻግረዉ ገበያ ሄደው ውለው ሲመለሱ ተማሪዎች ወንዞችን ተሻገረው ት/ቤት ሂደው ሲመለሱ ከብቶች ወንዞችን ተሻግረው ለግጦሽ ሂደው ሲመለሱ ስዎች ወንዞችን ተሻማረው ፍርድ ቤት ዉለው ለቀሶ ደርስዉ ሲመለሱ ወንዞች ሞልተዉ ሲያገ፫ቸው እቤታቸው ሳይመለሱ የሚያድሩና ዉሀው ሲጎድል የሚመለሱ በውሀዉ ሙላትም የሚወሰድም የሚሞቱም ብዙ ሰዎችና እንስሳት ስለነበሩ ይህንን ችግር ማህበሩ በመረዳት ይህንን ችግር በሚያደርሱ በተለያዩ ወንዞች ላይ ስዉና እንስሳ የሚያሻግሩ  የብረት ድልድዮች በመስራት ከላይ ከተገለጹት ችግሮች ህብረተስቡ እንዲገላገል ማድረጉ ሌላው የማህበሩ አስተዋጽዖ ነው፡፡

ስለዚህ በ 1990 ዓ/ም በወርሃ ነህሴ የተመሰረተው ፀረ ወባ የዛሬው ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” “በጋራ ለዉጥ እናምጣ” “የኛን ችግር ለመፍታት ከ እኛው እንጀምር ” በሚሉ መርሆች አማካኝነት ከላይ የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ማህበራዊ ችግሮች ያቃለለ በማቃለል ላይ የሚገኝ ማህበር ስለሆነ ይህንን የማህበሩ አላማ ተረድተን በበጎ ፈቃደኝነት ማንኛችንም ኢትዮጽያውያን ለማህበሩ ድጋፍ ልናደርግለት ይገባል፡፡

እኔም ማህበሩ ከመመስረቱ ጀምሮ ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባሮች ከመጀመሪያዉ እስከ መጨረሻዉ በሁሉም ክንዋኔዎች በበጎ ፈቃደኝነት በአባልነት ስላለሁበት ”ማን ያዉራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ” ስለሆነ ይህንን የማህበሩን ታሪክ በአጭሩ ለመጻፍ ሞክሬያለሁ፡፡