logo

Jan 10 2025

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ከግሎባል ፈንድ እና ጤና ሚኒስቴር ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር ከጤና ሚኒስቴር እና ግሎባል ፈንድ ጋር School and Community Based social Behavioral Change to reduce Malaria Burden in Ethiopia የተሰኘ ፕሮጀክት በ13 ክልሎች በ 49.7 ሚሊዮን ብር ለመተግበር ስምምነት ላይ ደረሰ ፡፡ ፕሮጀክቱ በዋናነት በኢትዮጵያ የወባ ጫናን ለመቀነስ በትምህርት ቤቶች እና ማኅበረሰብ ተኮር የባህሪ ለውጥ በወባ ህክምና እና ምርመራ እንዲሁም የወባ ትንኘ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በማኅበሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና በወባ ኤክስፐርት የፕሮጀከት ትግበራ እቅድ ቀርቧል፡፡ በቀረበው እቅድ ላይም የግሎባል ፈንድ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ አኒሾ እና በጤና ሚኒስቴር የወባ እና ሌሎች ቬክተር ወለድ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ኃላፊ አቶ ጉዲሳ አሰፋ አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡በቀጣይም የተሰጡ አስተያቶች ተካትተው ከሚኒስትሪው ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ወደ ፕሮጀክት ትግበራው ከመገባቱ በፊት ቀጣይ ዙር ውይይት ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution