logo

Feb 12 2025

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ከአዋሽ ባንክ ጋር የአጋርነት ሁለተኛ ዙር ውይይት አካሄደ::

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ከአዋሽ ባንክ ጋር የአጋርነት ሁለተኛ ዙር ውይይት አካሄደ::

የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ጌትነት ፤የፋይናንሥና አሥተዳደር ዳይሬክተር አቶ አለምሰገድ ፈለቀ እና የሃብት አሰባሰብ እና የአባላት ማበራከት አሥተባባሪ አቶ አድማሱ ሊበን እንዲሁም የማኅበሩ ሁለት የተግባቦትና አጋርነት ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡ ፡ ከአዋሽ ባንክ በኩል አቶ ቴዎድሮስ ታዲዮስ የፓርትነርሺፕ ማኔጅመንት ማኔጀር፤አቶ መብራቱ አበበ የሃይማኖት ተቋማት ኢንተርናሽናል ኤጀንሲ እና ኤምባሢ ዲቪዥን ማኔጀር እና ሌሎች የባንኩ ባለሙያዎች ተሣትፈዋል፡ ፡

ውይይቱም በዋናነት በሁለቱ ተቋማት መካከል በሚደረግ ሥትራቴጅክ አጋርነት ላይ ያተኮረ ሢሆን በትውልድ ግንባታ ላይ ያተኮረ ዘርፈብዙ የባህሪ ለውጥ ፕሮጀክት በመቅረፅ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ በጋራ ለመሠራት በሀሣብ ደረጃ ሥምምነት ላይ ተደርሧል ፡ ፡ በመጨረሻም ከሁለቱም ድርጅቶች የተውጣጡ ባለሙያዎችን በማሣተፍ ፕሮጀክት ለማዘጋጅት በመሥማማት ውይይቱ ተጠናቋል።

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution