logo

Feb 12 2025

ከውጭ ሃገር በመጡ ባለሙያዎች ሥልጠና ተሠጠ::

#ዜና HDAMA

ጥር 28 /2017 ዓ/ም ከExpertise France በመጡ የፕሮጀክት እና የፋይናንሥ ባለሙያዎች ሠናይ ፕሮጀከት ሥር ለሚገኙ የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር ሠራተኞች ሥልጠና ተሠጠ፡፡

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር ከExpertise France ጋር በመተባበር Sennay- Reducing Malaria Burden among Seasonal Mobile Workers የተሠኘ ፕሮጀክት በአማራ ክልል ባሉ 5 ወረዳዎች በመተግበር ላይ ይገኛል ፡፡

ፕሮጀክቱ በዋናነት ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው ተብለው ለተለዩ፣በልማት ቀጠናዎች ትላልቅ የእርሻ ጣቢያዎች ላይ የሚሠሩ ተንቀሳቃሽ የማኅበረሠብ ክፍሎችን ከወባ በሽታ መከላከል እንዲሁም ከወባ ምርመራና ህክምና እሥከ በሽታ ክትትልና ምላሽ መሠጠት ድረሥ ይሠራል፡፡

የማኅበሩ ምክትል ዋና ዳይሬከተር አቶ አክሊሉ ጌትነት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የሠናይ ፐሮጀከት ማናጀር አቶ ሥዩም መንገሻ አጠቃላይ በፕሮጀክቱ የተሠሩ ተግባራትንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በማንሣት ዘገባ አቅርበዋል፡፡በማሥከተልም ከExpertise France የመጡ የፐሮጀክት እና የፋይናንሥ ባለሙያዎች በፕሮጀክት በጀት አያያዝ ዙሪያ ሥልጠና ሠጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ለአሠልጣኞች ባህላዊ የአንገት ልብሥ እና ቦርሣ በማህበሩ አስተዳደር በኩል ሥጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution