logo

Apr 30 2026

የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በአማራ ክልል ልዩ እውቅናና ሽልማት አገኘ!

የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በአማራ ክልል ልዩ እውቅናና ሽልማት አገኘ
ባህር ዳር – የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ በክልሉ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባዘጋጀው የእውቅናና ምስጋና መድረክ ላይ፤ የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር የላቀ አፈጻጸም ላላቸው ድርጅቶች የሚሰጠውን ልዩ ሽልማትና የምስክር ወረቀት በዛሬው ዕለት ተቀበለ።
በክልሉ መዲና ባህርዳር በተከናወነው በዚህ መድረክ ላይ በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከ130 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ ማኅበሩ በተለያዩ መስፈርቶች ተገምግሞ ካሳየው ውጤታማ የሥራ አፈጻጸም አንጻር በልዩ ተሸላሚነት ሊመረጥ ችሏል።

ይህ ሽልማት ማኅበሩ በክልሉ የጤና ዘርፍ ላይ የወባ በሽታን ለመከላከል፣ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ፣ተደራሽ ባልሆኑና የፀጥታ ችግር በተከሰተባቸው ክልሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ሕይወት አድን መድኃኒቶችን በማሰራጭትና የጤና ተቋማትን በማጠናከር ለሚያከናውናቸው ሰብዓዊ ተግባራት የተሰጠ ትልቅ እውቅና መሆኑ ተገልጿል።
ሽልማቱን አስመልክቶ በክልሉ የማህበሩ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስተባባሪ አቶ ጋሻው ድሌ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ ውጤቱ የተመዘገበው በማኅበሩ የስራ ሃላፊዎች ፣ ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች፣አጋሮችና በደጋፊ አካላት የተቀናጀ ጥረት መሆኑን ጠቅሰው፤ ለሁሉም የማኅበሩ አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ማኅበሩ በቀጣይም በክልሉ የሚሰራቸውን የጤናና የልማት ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በመድረኩ ላይ ተመላክቷል።

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution