logo

Jul 06 2026

የጤና፣ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በተንቀሳቃሽ ሠራተኞች ላይ ያተኮረ የወባ መከላከል፣ ምርመራና ሕክምና ሥራዎችን እያከናወነ ነው

የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር “ሰናይ” በተሰኘው ፕሮጀክቱ አማካኝነት በአማራ ክልል በ5 ወረዳዎች በሚገኙ ሰፋፊ እርሻዎች እና የልማት ቀጠናዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል። ማኅበሩ በእነዚህ አካባቢዎች ለሚገኙና ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ ጊዜያዊና ተንቀሳቃሽ ሠራተኞች አጠቃላይ የወባ መከላከል ተግባራትን፣ የምርመራና የሕክምና አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ላይ ነው።

በአሁኑ ወቅትም በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ በሚገኘው ላይበር እርሻ ልማት ውስጥ፦

📌 የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታ የቁጥጥር ሥራዎች በስፋት እየተሰሩ ነው፤

🩸 ፈጣን የወባ ምርመራና የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።

#ጤና_ልማትና_ፀረ_ወባ #ሰናይ_ፕሮጀክት #የወባ_መከላከያ #ጃቢጠህናን #ላይበር_እርሻ

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution