logo

Oct 14 2026

የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በባህር ዳር ተካሄደ

ባህር ዳር — መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም. የጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በአብክመ ጤና ቢሮ አዳራሽ አካሄደ። በምረቃው ላይ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት የማኅበሩን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጉልተዋል።

የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር  አበረ ምሕረቴ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፤ በወባ፣ በስነ-ተዋልዶ፣ በጾታዊ ጥቃትና በትንባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት ተዳስሰዋል። በተለይም በፀጥታ ችግር ወቅት ከጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ለወረዳዎች የተደረገው የመድኃኒት አቅርቦት ድጋፍ በዋና ስኬትነት ተጠቅሷል።

ጉባዔው የቀረቡትን የ2018 የክንውን እና የኦዲት ሪፖርቶች፣ የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያውን፣ የ2019 ዕቅድን እንዲሁም የማኅበሩን የጋራ መዝሙር በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

በስብሰባው ማጠናቀቂያ ለአጋር አካላትና አስተባባሪዎች የምስክር ወረቀትና እውቅና ተሰጥቷል። ከክላስተሮች ከፍተኛ አፈጻጸም ላሳዩት፡-

  1. አቶ ግዛቸው ባይሌ (ደቡብ ጎንደር) ክላስተር
  2. አቶ አብጠው ከበደ (እነማይ) ክላስተር
  3. አቶ አገኘሁ ሙሉነህ (አዊ) ክላስተር እንዲሁም ለክልል አስተባባሪ አቶ ጋሻው ድሌ የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ለሠራተኞች፣ ለአጋር አካላትና ለአባላት ምስጋና አቅርበዋል።

በቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና በጸሐፊ ወ/ሮ አስካለ አድማሱ መሪነት የተካሄደው ይህ ጉባዔ፣ 456,000 አባላትን የሚወክሉ ተሳታፊዎች የታደሙበት ሲሆን፤ ተቋማዊ አቅምን፣ ገጽታንና ገቢን በማሳደግ ላይ ያተኮሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ በስኬት ተጠናቋል።

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution