logo

Dec 13 2024

በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ 71 ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖረት ተደርጓል ተባለ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ከ 71 ሺህ በላይ አዳዲስ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጉን የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሰታውቋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከሌሎች ሳምንታት አንፃር 4.2 በመቶ የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል ፡፡

በበጀት አመቱ ከ 1 ሚለዮን 1መቶ 46 ሺህ በላይ የወባ ህሙማን ሪፖርት መደረጉንም አንስተዋል፡፡

ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ አመት ጋር ሲነፃፀር የ67 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

ስርጭቱን ለመቆጣጠር ጤና ጣቢያ መር ማህበረሰብ አቀፍ አካባቢ ቁጥጥር ስራ አየተሰራ መሆኑ ተገልጧል

በዚህም ከ 6 መቶ በላይ በሆኑ ጤና ጣቢያዎች ማህበረሰብ አቀፍ አካባቢ ቁጥጥር ስራዎች መስራት መጀመሩን የፕሮግራም አስተባባሪው ተናገረዋል፡፡

(ኢትዬ ኤፍ ኤም)

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution