logo

Feb 12 2025

የኢትዮጵያ ወባ ማሥወገድ ጥምረት ቦርድ መር ድርጅት ምሥረታ ።

#ዜና HDAMA#

የኢትዮጵያ ወባ ማስወገድ ጥምረት ዓላማው በመላው ኢትዮጵያ የወባ በሽታን ለማጥፋትና የጤና ውጤቶችን ለማሻሻል የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ጥረቶችን አንድ ለማድረግ ነው።

ጥር 15 /2017 በኢሊሊ ሆቴል በጋራ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን የውይይቱ መከፈቻ ንግግር በዶ/ር አበረ ምሕረቴ ተጀምሮ የፕሮግራሙን ትውውቅ ደግሞ አቶ አሸብር ወጋየሁ አድርጓል።የቦርድ መር ድርጅቱ ሥያሜና ዓርማ ላይ መወያየትና ማጽደቅ፣ቦርድ መር ድርጅቱን ለመመሠረት መነሻ የሆኑ ምክንያቶች ማፅደቅ፣የቦርድ መር ድርጅቱ አላማ ማፅደቅ፣የቦርድ መር ድርጅቱን የቦርድ አባላት መምረጥ እና የሥራ ድርሻ መሠየም በዋናነት የተነሡ አጀንዳዎች ናቸው።

በጤና ሚኒሥቴር ባስቀመጠው ወባን የማጥፋት ሥትራቴጂ መሠረት በማድረግ በዚህ መሥክ የሚሠሩ የተለያዩ የሢቪል ማህበረሠብ ድርጅቶችን የተናጥል ጥረት አንድ በማድረግ ትልቅ ውጤት ለማምጣት የታሠበ ነው፡፡

በወባ ማሥወገድ ዙሪያ ካስፈፃሚና ቁልፍ አጋር ድርጅቶች ጋር መተባበር፣የአባል ድርጅቶች ወባን በማሥወገድ ዙሪያ የማህበረሠብ ንቅናቄና ግንዛቤ ሥራዎችን ማገዝና ማጠናከር፣ለወባ ማሥወገድ ሥራ የሚያሥፈልግ ሀብት ማሠባሠብና ለአባላቱ ድጋፍ ማድረግ፣በአገር እና በዓለም አቀፍ የወባ ማሥወገድ ጥረቶች ተዋናይ ከሆኑ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር አጋርነት መፍጠር እና ሌሎችንም ጨምሮ በአጠቃላይ 9 ዋና ዋና የሚባሉ አላማዎች ላይ በሥፋት በመወያየት አፅደቀዋል።

የሥራ አመራር ቦርዱ የአገልግሎት ዘመን 4 ዓመት ሢሆን በጥምረቱ መተዳደሪያ ደምብ አንቀጽ 7 መሠረት የአገልግሎት ዘመናቸው 4 አመት የሆነ 5 የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ምርጫ ተካሄዷል ።የሥራ አመራር ቦርድ ሠብሣቢ፤ ምክትል ሠብሣቢ፤ፀሐፊ እና አባል በመሆን የተመረጡ ሢሆን የክቡር ዶ/ር አበረ ምሕረቴ ሠብሣቢ፣ ዶ/ር ዘላለም ከበደ ከፌኔ ምክትል የቦርድ ሠበሣቢ ና ዶ/ር አለማየሁ መኮንን ለማ የቦርድ ፀሐፊ ሢሆኑ ቀሪዎቹ 2ቱ አባል በመሆን ተመርጠዋል።

በማሥከተለም የኢትዮጵያ ወባ ማሥወገድ ጥምረት መተዳደሪያ ደንቡ ላይ በመወያየት የጥምረትና በጎ አድራጎት ድርጅቶች ምዝገባና አሥተዳደር አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ጉዳዮች የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ባገናዘበ መልኩ የጥምረቱ መተዳደሪያ ደንብን በአዋጁ መሠረት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

ሥያሜውን በተመለከተም “የኢትዮጵያ ወባ ማሥወገድ ጥምረት” /በአማርኛ/ ETHIOPIA END MALARIA NETWORK (EEMN) በእንግሊዝኛ/ በሚል ስያሜ እንዲፀድቅ በሙሉ ድምፅ ተወስኗል፡፡ዓርማውም ድርጅቱ ጋር በተዛመደ ሥዕሉ እንደ ስሙ (“የኢትዮጵያ ወባ ማስወገድ ጥምረት”) በሚል እንዲቀየረ በሙሉ ድምፅ ተወሥኗል፡፡

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution