logo

Apr 05 2025

ጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር 840 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የህክምና ግብአቶችን አሰራጨ!

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር በአማራ ክልል ተደራሽ ባልሆኑና የፀጥታ ችግር በተከሰተባቸው ዞኖች በሚገኙ ጤና ተቋማት አስፈላጊ የሆኑ ሕይወት አድን የመደኃኒት ግብዓቶችን አሰራጨ።

ማኅበሩ ለእነዚህ አሥቸኳይ ፍላጎቶች ምላሽ ለመሥጠት ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የባህር ዳር ቅርንጫፍ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ከታህሣሥ 2016 ዓ. ም ጀምሮ ለ29ኛ ዙር የትራንስፖርት አገልግሎት በማካሄድ በብር 840 ሚሊዮን የሚገመቱ የህክምና ግብዓቶችን አጓጉዟል።በምስራቅ ፣ምዕራብ፣ ሰሜን ጎጃምና አዊ፤ ደቡብ፣ሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ በአጠቃላይ ከ ዘጠኝ በላይ ዞኖች ባሉ 134 ወረዳዎች በሚገኙ 649 የጤና ተቋማት ስርጭት አካሂዷል። 9 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችንም ተጠቃሚ አድርጓል።

በክልሉ በተከሠተው ግጭት የጤና ዘረፉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሡ አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሣቁሦችን ለጤና ተቋማት ለማሠራጨት ከፍተኛ ችግር የፈጠረ ቢሆንም ማኅበሩ ከ Chemonics International እና USAID ጋር በጥምረት እንዲሁም ከማኅበሩ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ባህርዳር፥ደሴ እና ጎንደር ከሚገኘው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መድኃኒት ማከማቻ መጋዘን የፀረ-ወባ፣ የፀረ ኤች አይ ቪ፣ የቲቢ፣ የክትባት፣የጨቅላ ህፃናትና እናቶች፣የወሊድ መቆጣጠሪያ፣ እና ሌሎች ሕይወት አድን መድኃኒቶችን አጓጉዟል፡፡

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር ፈጣን ምላሽ በሚያገለግለው ማህበረሰብ ላይ በጎ ተጽዕኖ አሣድሯል። ማኅበሩ በዚህ ወሣኝ ወቅት አሥፈላጊ የጤና ተቋማትን በህይወት አድን የመድኃኒት ግብዓቶች ተደራሽ አድርጓል።

ይህን በተመለከተም የአዴት ሆሥፒታል ሥራ አሥኪያጅ አቶ በዛብህ አካሉ ልምዳቸውን እንደሚከተለው አካፍለዋል።

“በአሥፈላጊ መድኃኒቶች ሙሉ በሙሉ መሟጠጥ ምክንያት አገልግሎት ለመስጠት ካለመቻላችንም ባሻገር ታካሚዎቻችንም በእጅጉ ችግር ላይ ወድቀዋል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ባቀረበነው የዕርዳታ ጥሪ መሠረት ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር አሥፈላጊውን መድሃኒት ለማጓጓዝ በፍጥነት ተሽከርካሪ በማቅረብ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅርንጫፎች በመነሣት ለ በርካታ ጤና ተቋማት የቀጥታ ሥርጭት በማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ሕይወትን የመታደግ ሥራ ሠርቷል። በዚህም ታካሚዎቻችን መድኃኒት ሢወሥዱ ፊታቸው ላይ የነበረውን ደሥታ በቃላት ለመግለጽ ያዳግታል፡፡ ምሥጋና ለጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር ዳግመኛ እንደተወለድን ቆጥረነዋል፡፡”

ይህ ከልብ የመነጨ ምሥክርነት ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር በችግሮች እና ፈተናዎች መካከል የጤና አጠባበቅ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት ያሣያል።

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution