logo

Oct 16 2024

ሕይወት አድን የመድኃኒት ግብአቶችን የቀጥታ ሥርጭት

ሕይወት አድን የመድኃኒት ግብአቶችን የቀጥታ ሥርጭት

ሕይወት አድን የመድኃኒት ግብአቶችን የቀጥታ ሥርጭት

በአማራ ክልል በተከሠተው ግጭት የጤና ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሡ አሥፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሣቁሦችን ለጤና ተቋማት ለማሠራጨት ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል።

ለእነዚህ አሥቸኳይ ፍላጎቶች ምላሽ ለመሥጠት ጤና፣ ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ እና ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የባህር ዳር ቅርንጫፍ በርካታ የዕርዳታ ጥያቄዎች ቀርበውለታል። የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር ዳይሬክተር ክቡር /ዶ/ር አበረ ምሕረቴ እነዚህን ቅርንጫፎች በመጎብኘት አፋጣኝ እርምጃ ወሥደዋል።

ከታህሣሥ 2016 ዓ. ም ጀምሮ ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኀበር በ3 ዙር የቀጥታ ሥርጭት (Last mile delivery) አድርጓል፡፡ ይህ ጅምር በ5 ዞኖች ማለትም በምሥራቅ ጎጃም ፣በምዕራብ ጎጃም ፣በደቡብ ጎንደር ፣በሠሜን ጎጃም እና በአዊ በሚገኙ 35 ወረዳዎች 156 የጤና ተቋማትን በተሣካ ሁኔታ ተደራሽ አድርጓል። በዚህም የ3ዙር የቀጥታ ሥርጭት አገልግሎት ማኅበሩ 787,710 ብር ወጭ በማድረግ ግምታቸው 41,897,493.60 የሆኑ የህክምና ግብዓቶችን ተደራሽ የያደረገ ሢሆን እነዚህ ጥረቶች በክልሉ ውሥጥ የጤና አጠባበቅ ተደራሽነትን ወደ ነበረበት ለመመለሥ እና ህይወትን ለመታደግ ወሣኝ እርምጃዎች መሆናቸውን አመላክተዋል።

Like

Comment

Share

admin

Leave A Comment

Our Maps

© 2024 Copyright by Merciitsolution